በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኦገስት 2 በተካሔደው የ3000 ሜትር የመሰናክል ሩጫ ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የብር ሜዳል ባለቤት ለመሆን በቅቷል።

ጉዳፍ ፀጋይ በሴቶች 5000 ሜትር ሩጫ ውድድር 143887 በሶስተኛ ደረጃ መጨረስ የነሐስ ሜዳል አሸናፊ ሆናለች።
በእዚሁ የ5000 ሜትር ውድድር እጅጋየሁ ታየ 14:41:24 በሆነ ውጤት አምስተኛ ሆና ስታጠናቅቅ ሰንበሬ ተፈሪ 14:45:11 በመጨረስ ስድስተና ሆናለች።
የ5000 ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ተይዞ ይገኛል።
ለተሰንበት እ.አ.አ በ2020 በቫሌንስያ ስፔይን የተካሔደውን የ5000 ሜትር ውድድር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ ያጠናቀቀችው 14:06:62 በሆነ ውጤት ነው።

