ኢትዮጵያ በዘንድሮው የቶኪዮ ኦሎምፒክ እስካሁን ከተካሄዱ ውድድሮች ወርቅ ያገኘችው በወንዶች 10 ሺህ ሩጫ ብቻ ነው።
ትናንት በተካሔደው የሴቶች ማራቶን ውድድር ሮዛ ደረጀ 2:28:38 በማጠናቀቅ አራተኛ በመሆን ጨርሳለች። ብርሃኔ ዲባባና ዘይነባ ይመር ውድድሩን ሳያጠናቅቁ አቋርጠው ወጥተዋል።
በዚህ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ ከብርና ነሃስ በላይ የወርቅ ሜዳልያ የምትጠብቀው በ10 ሺህ ውድድር ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋ እንዳደረገው ዛሬ በአውስትራሊያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 8:45pm ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ ተጠባቂ ውድድር ኢትዮጵያ በ10 ሺ ሜትር ፍፃሜ ለተሰንበት ግደይ፣ ፅጌ ገ/ሰላማና ፀሀይ ገመቹ አማካኝነት ትወከላለች።
በርካታ ኢትዮጵያውያን ውድድሩን በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ በሶሻል ሚዲያ እየገለፁ ይገኛሉ።
[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]

