ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የማጣሪያ ዙር ውድድሮችን በአሸናፊነት አጠናቀቁ

*** ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳል በተስፋ የምትጠብቅበት የወንዶች 10000 ሜትር የፍጻሜ ውድድር ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይካሔዳል

Tokyo 2020 Olympic Games

Ethiopia's Lamecha Girma (C). Source: Getty

በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ውድድር ሠንጠረዥን ተከትሎ በተጀመረው የ3000 ሜትር ወንዶች የማጣሪያ ዙር የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቀዳሚና ተከታይነት ለቀጣይ ዙር አልፈዋል።

በውድድሩም፤

  • ለሜቻ ግርማ 8:09:83 በመጨረስ ከምድቡ አንደኛ ሆኖ ሲያልፍ
Tokyo 2020 Olympic Games
Ethiopia's Lamecha Girma (C) competes ahead of Japan's Ryuji Miura (L) in the men's 3000m steeplechase heats during the Tokyo 2020 Olympic Games on July 30,2020 Source: Getty
  • ጌትነት ዋለ በኬንያዊው ኪቢዎት ተቀድሞ 8:12:55 በማጠናቀቅ በሁለተኛ ደረጃነት ለቀጣይ ዙር ውድድር ተሻግረዋል። 
Tokyo 2020 Olympic Games
Kenya's Abraham Kibiwot (R) and Ethiopia's Getnet Wale (2R) compete in the men's 3000m steeplechase heats during the Tokyo 2020 Olympic Games on July 30, 2021. Source: Getty
  • በሴቶች የ800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ሀብታም ዓለሙ 2:01:20 ጨርሳ በሁለተኛነት ከምድቧ አልፋለች።
Tokyo 2020 Olympic Games
(From L) Hungary's Bianka Bartha Keri, Ethiopia's Habitam Alemu and USA's Athing Mu competes in the women's 800m heats during the Tokyo 2020 Olympic Games. Source: Getty

ዛሬ ማምሻውን በአውስትራሊያ ሰዓት አቆጣጠር 9፡30pm ጀምሮ የወንዶች 10000 ሜትር የፍጻሜ ውድድርና የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ውድድሮች ይከናወናሉ።

በወንዶች 10000 ሜትር ፍጻሜ ተወዳዳሪዎቹ ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሰለሞን ባረጋና በሪሁ አረጋዊ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳል የማስገኘት ዕድል ሰፊ ሆኖ ይጠበቃል። 

በሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ተፎካካሪዎቹ ጉዳፍ ፀጋይ፣ ሰንበሬ ተፈሪና እጅጋየሁ ታየ በማጣሪያ ዙር ውድድራቸው ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሸጋግራቸውን ውጤቶች በማግኘት ያልፋሉ ተብሎ ከፍተኛ ግምት ተጥሎባቸዋል።

በቶኪዮ ኦሎምፒክ መክፈቻ ሥነ ሥር ዓት ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውለብሎ የነበረው አብዱልማሊክ ሙክታር በ50 ሜትር ነፃ የቀዘፋ ዋና ማጣሪያ ይወዳደራል። 

 


1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now