ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ለኦሎምፒክ ሜዳል የማጣሪያ ወድድሮችን እያሸነፉ ነው

*** የሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ማጣሪያ ማምሻውን ይካሔዳል

Tokyo 2020 Olympic Games

Ethiopia's Gudaf Tsegay crosses the finish line to win a race in the women's 5000m heats during the Tokyo 2020 Olympic Games on July 30, 2021. Source: Getty

ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በ800 እና 5000 ሜትሮች የማጣሪያ ውድድሮችን በአሸናፊነት እያለፉ ነው።

ትናንት ጁላይ 30 በቶኪዮ ኦሎምፒክ ስታዲየም በተካሔደው የ5000 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ውድድሮች፤

  • ሰንበሬ ተፈሪ  14:48:31
  • እጅጋየሁ ታየ 14:48:52
  • ጉዳፍ ፀጋይ 14:55:74 በሆነ ውጤት ሰኞ ኦገስት 2 ምሽት ለሚካሔደው የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል።

የ5000 ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ተይዞ ይገኛል።

ለተሰንበት እ.አ.አ በ2020 በቫሌንስያ ስፔይን የተካሔደውን የ5000 ሜትር ውድድር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ ያጠናቀቀችው 14:06:62 በሆነ ውጤት ነው።

Tokyo 2020 Olympic Games
(From L) Ethiopia's Ejgayehu Taye and Ethiopia's Senbere Teferi compete in the women's 5000m heats during the Tokyo 2020 Olympic Games on July 30, 2021. Source: Getty

በሴቶችና በወንዶች የ800 ሜትር ውድድሮች በትናንትናው ዕለት ተወዳዳሪ ከነበሩት ውስጥ፤

  • ሃብታም ዓለሙ 2:01:20 በመጨረስ ዛሬ ማምሻውን ለሚካሔደው የግማሽ ፍፃሜ ውድድር አልፋለች
  • ነፃነት ደስታ 2:01:98 በማጠናቀቅ ለቀጣዩ ውድድር ሳታልፍ ቀርታለች
  • በወንዶች ውድድር መለስ ንብረት 1:47:80 በመጨረስ በለስ ሳይቀናው ከውድድሩ ተሰናባች ሆኗል።

 


1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now