በ10000 ሜትር የቶኪዮ ኦሎምፒክ የሩጫ ውድድርን በአንደኛ ደረጃ አሸናፊነት የተወጣው አትሌት ሰለሞን ባረጋ የወርቅ ሜዳል ተቀበለ።
ለኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የመጀመሪያ የሆነውን የወርቅ ሜዳል ያስገኘው ሰለሞን የ10 ሺህ ሜትር ውድድሩን በአሸናፊነት የደመደመው 27:43:22 በመጨረስ ነው።

ትናንት ማምሻውን በተካሔደው የሴቶች 800 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ዘርፌ ወንድማገኝ 92001 በሆነ ውጤት፤ እንዲሁም ሃብታም ዓለሙ 1:58:40 በማጠናቀቅ የዩናይትድ ስቴት ሷን ሙ አቲንግ ተከትላ ከምድቧ በሁለተኛ ደረጃ አሸንፋ ለፍጻሜ ውድድር አልፋለች።

የ800 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ኦገስት 3 ማክሰኞ ምሽት 10:25pm ይካሔዳል።
በወንዶች 800 ሜትር ውድድር ለማጣሪያ ያለፈ አትሌት ባለመኖሩ ኢትዮጵያ በወንዶች 800 ሜትር ውድድር አትሳተፍም።
በሴቶች 3000 የመሰናክል ሩጫ ውድድር መቅደስ አበበ 9:23:95 በማጠናቀቅ ኦገስት 4 ከምሽቱ 21:00 ለሚካሔደው የፍፃሜ ውድድር አልፋለች።

ኢትዮጵያ ለቶኪዮ ኦሎምፒክ በዘጠኝ የውድድር መስኮች 34 ተወዳዳሪዎችን አሰልፋለች።

