SKIP TO MAIN CONTENT

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና ሰባት የሲቪል አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ

*** ከመከላከያ ሕወሓትን ተቀላቅለው የነበሩ ከፍተኛ መኮንንኖችም ተይዘዋል።

Abay Woldu
Abay Woldu, former President of Tigray regional state Source: Getty

2 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሰባት የሲቪል አመራሮችና ከመከላከያ ከድተው ሕወሓትን የተቀላቀሉ አመራሮችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና እርምጃ የተወሰደባቸውን መኮንኖች ዝርዝር የመከላከያ ሠራዊት ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።

በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-

1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረና አሁን የጁንታው ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረ

2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበረና በጡረታ ከተሰናበተ በኋላ ጁንታውን የተቀላቀለ

3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች

4ኛ – ሁለት መስመራዊ መኮንኖች

5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ ከድቶ ወደ ጁንታው የተቀላቀሉ ናቸው።

በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ገልፀዋል።

እነዚህም

1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ

2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ

3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ

4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ

5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ

6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ

7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሁለት ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ኢዜአ


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now