በሕዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን መካከል የተካሄደው ድርድር ያለ ስኬት አበቃ

በሕዳሴ ግድብ ላይ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳንን ያማከለ መለስተኛ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በቅርቡ ይጠራል።

GERD talks

Renaissance Dam Source: Courtesy of SUNA

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳንን በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ለማሸማገል ከመከረ በኋላ ጉዳዩ በአፍሪካ ሕብረት እንዲታይ ማሳሰቡ ይታወሳል። ይህንኑ የመግሥታቱ አገራት ድርጅት ምክረ ሃሳብ ተከትሎም ለ11 ቀናት በውኃ ሚኒስትሮች አማካይነት የተካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር ከስምምነት ላይ ሳይደርስ አክትሟል።

የድረድሩን ሂደትና ክሽፈት አስመልክቶ በኢትዮጵያ በኩል ለአፍሪካ ሕብረትና መሪዎች ቢሮ ሪፖርት ተሰናድቶ እንደሚላክና የመሪዎችን መመሪያዎች ተከትሎም ቀጣይ ውይይቶች እንደሚኖሩ የውኃና መስኖ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በቲዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። 

GERD talks
Source: Seleshi Bekele

የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስቴርም በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፤

"ለ11 ቀናት በአፍሪካ ሕብረት አማካይነት የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ሙሌትና የግድቡን ሥራ ክንውን አስመልክቶ የሶስቱ አገራት የውኃ ሚኒስትሮች፣ የአገራት ተወካዮችና ታዛቢዎች በተገኘኙበት የተካሔደው ድርድር ጁላይ 13 ተጠናቅቋል "

"የሚኒስትሮቹን ስብሰባ ተከትሎ የሶስቱ አገራት ቴክኒክና የሕግ ኮሚቴዎች ክለሳ ዋነኛ በሆኑት የሕዳሴ ግድብ ሙሌትና የግድቡ ሥራ ክንዋኔ ላይ ልዩነቶች ዕልባት ሳያገኙ መቀጠላቸው ተንጸባርቋል"

"በስብሰባው ማብቂያ ላይም ሚኒስትሮቹ እያንዳንዱ አገር ለቀጣዩ ድርድር መሸጋገሪያ ሆኖ መለስተኛ የአፍሪካ ጉባኤን ለማካሔድ የመጨረሻ ሪፖርቱን ለወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ፕሬዚደንት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ተስማምተዋል" ሲል አስታውቋል። 

የድርድሩን ሂደት አስመክልቶ ሱዳን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ፕሬዚደንት በላከችው ሪፖርቷ በድረድሩ ወቅት "ሁነኛ በሆኑ ጉዳዮች" ላይ "መጠነኛ መሻሻል" መታያታቸውን አስፍራለች።

ሱዳን ከሪፖርቷ ጋር "በሶስቱ አገራት ተቀባይነት የሚኖረው ሚዛናዊና ፍትሓዊ" ረቂቅ ስምምነት አያይዛ መላኳን አስታውቃለች። 

 በቀጣይነትም የሶስቱን አገራት ሪፖርትና አማራጭ የስምምነት መፍትሔ ምክረ ሃሳቦች ከተቀበሉ በኋላ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ፕሬዚደንት የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት መለስተኛ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤን ከመጥራታቸው በፊት የሶስቱን አገራት መሪዎችና የአፍሪካ ቢሮ ኃላፊዎችን ደውለው እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል። 

 

 

 

 

 

 

 


2 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now