የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ነገ ኢትዮጵያ ይገባሉ፤ ከባለስልጣናትም ጋር ይነጋገራሉ

*** ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ፈጣን የኮቪድ-19 መመርመሪያ ለሁሉም አውስትራሊያውያን በነፃ እንደማይታደል አስታወቁ፤ የሌብር ፓርቲ በነፃ እንዲታደል ጠየቀ

News

Ambassador Jeffrey Feltman, U.S. Horn of Africa envoy. Source: Getty

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ነገ ሐሙስ ዲሴምበር 6 አዲስ አበባ እንደሚገቡና በሰላማዊ መፍትሔ ፍለጋ ላይ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ባለፈው ሳምንት የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ የሕወሓት ወደ ትግራይ ክልል መመለስና የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ያለመዝለቅ ውሳኔ ሁለቱ ባላንጣዎች ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ለድርድር እንዲቀርቡ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።  

ይሁንና በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የአየር ጥቃቶች አልተቋረጡም። እንዲሁም፤ የትግራይ ተዋጊዎች ከመንግሥትና አጋር ተዋጊዎች ጋር የተለያዩ አነስተኛ ግጭቶች እያደረጉ መሆኑ ተዘግቧል።  

***

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የኮሮናቫይረስ ፈጣን መመርመሪያ ለሁሉም ኣውስትራሊያውያን በነፃ እንደማይታደል ዛሬ ረቡዕ ዲሴምበር 05 አስታውቀዋል። ሆኖም የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልባኒዚና በርካታ የተለያዩ ድርጅት መሪዎች መመርመሪያው ለሁሉም አውስትራሊያውያን በነፃ እንዲታደል ጥሪያቸውን እያሰሙ ነው። 

በ2022 ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየመው ብሔራዊ ካቢኔ በገቢያቸው አንስተኛነት የቅናሽ ካርድ ያላቸው በርካሽ እንዲገዙ ድጎማ እንዲደረግላቸው ወስኗል። 

160 ሚሊየን ፈጣን መመርመሪያዎች (RATs) አውስትራሊያ ውስጥ በቅርቡ ይደርሳሉ። 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤ 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 35,054  ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የስምንት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ቪክቶሪያ ውስጥ 17,636 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 11 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

 ኩዊንስላንድ 6,781 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል።

ደቡብ አውስትራሊያ 3,493 በቫይረስ ተጠቅተዋል።

ታዝማኒያ 867 ሰዎች ተጠቅቶባታል።

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 810 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል።

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ here.

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

Find out what you can and can't do in your state or territory

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language

 

 

 

 


2 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now