ዩናይትድ ስቴትስ አዲስ የማዕቀብ ዒላማዋን በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ተሳታፊ መሪዎች ላይ አነጣጠረች

*** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግልፅ የምላሽ ደብዳቤ ለፕሬዚደንት ባይደን ላኩ

U.S. President Joe Biden (L) and Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed (R).

U.S. President Joe Biden (L) and Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed (R). Source: Getty

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ሴፕቴምበር 17, 2021 ሰሜናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቶ ያለው የረድኤትና ሰብዓዊ ቀውስ በእጅጉ እንዳሳሰባቸውና መዘዙም የኢትዮጵያንና የአፍሪካ ቀንድን ሰላም፣ ፀጥታና መረጋጋት ለስጋት የዳረገ መሆኑን በማመላከት አዲስ የማዕቀብ ማዘዣ አውጥተዋል።  

ማዕቀቡም በዩናይትድ ስቴትስ በጅሮንድና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክክር በሰሜን ኢትዮጵያ ሂደት ላይ ያለው ቀውስ እንዲስፋፋ ወይም እንዲራዘም ወይም ለተኩስ አቁም ስምምነት ወይም የሰላም ሂደት ላይ ሳንካ ፈጣሪና በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠርጣሪ የተባሉት ላይ እንዲያነጣጥሩ መመሪያ ሰጥተዋል። 

ይህንኑ የፕሬዘደንቱን መመሪያ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የኤርትራ መንግሥት፣ የአማራ ክልላዊ መንግሥትና የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሪዎችን በማመላከት ዩናይትድ ስቴትስ  "ሁሉም ግጭቱን እንዲያበቃ ወደ ድርድር እንዲገቡ" ጥሪ የምታደርግ መሆኗን ምክትል በጅሮንድ ዋሊ አዴየሞ ተናግረዋል።  

በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዚደንት ጆ ባይደን ሴፕቴምበር 17, 2021 በላኩት ግልፅ ደብዳቤ የኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ሂደት ጉዞ፣ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ 40 ሚሊየን ያህል ሕዝብጁን 21 2001 በመራጭነት ተሳትፎ በብልፅግና ፓርቲ ላይ ያለውን እምነት መግለፁንና ሕወሓት የግጭቱ መንስኤ መሆኑን አመላክተዋል።

አክለውም፤ ብሔራዊ፣ ሪጂናዊና ሉላዊ የፀጥታ ስጋቶች በአብዛኛው የዓለም ክፍሎች የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ጥቅሞችን የሚመለከት እንደሆነ በማመላከት "የእርስዎ አስተዳደር ሕወሓትን ተፃርሮ ስለምን ጠንካራ አቋም አልወሰደም?" ሲሉ ጠይቀዋል። 

ገዲብ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ለአ ዣንስ ፕሬስ እንደገለጡት አዲሱ ፓርላማ ኦክቶበር 4 ከመሰየሙ በፊት ግጭቱ በንግግር ዕልባት እንዲበጅለት የመንግሥታቸው ፍላጎት ቢሆንም ያ ይሆናል የሚል አመኔታ ግና እንደሌላቸው ገልጠዋል።   

በኤርትራ መንግሥትና በሕወሓት በኩል ለጊዜው ምላሻቸው አልተነገረም። 

ማዕቀቡ እንዴትና በእነማን ላይ እንደሚያርፍ በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። 


2 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now