SKIP TO MAIN CONTENT

ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ የጦር ኃይሎች ልዩ ረዳት ላይ እገዳ ጣለች

*** ኤርትራ "ፍፁም መሠረተ ቢስ ውንጀላ" ስትል አሌ አለች

The U.S. Treasury Department
The U.S. Treasury Department building in Washington, D.C. Source: Getty

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Skip to article content

የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት መምሪያ ትናንት ሰኞ ኦገስት 23 በኤርትራ የጦር ኃይሎች ልዩ ረዳት ጄኔራል ፊሊፖስ ወልደዮሃንስ ላይ ትግራይ ውስጥ በተፈጸመ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እጃቸው አለበት በሚል ሳቢያ እገዳ ጥሏል። 

መምሪያው እንዳስታወቀው በጦር ኃይሎች ልዩ ረዳቱ ላይ እገዳው የተጣለው የጅምላ ጭፍጨፋ፣ መጠነ ሰፊ ወሲባዊ ጥቃትና ሆን ተብሎ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጎዳና ግድያ ፍጸማዎችን ያካተተውን ሉላዊ ማግኒትስኪ የሰብዓዊ መብቶች የተጠያቂነት አንቀጽ ተከትሎ እንደሆነ አስታውቋል። 

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም በበኩላቸው "ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ በብርቱ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፣ ለግጭቱ መራዘምና የሰብዓዊ ቀውስ ክስተት ላይ የተሳትፉትን በመለየትና እርምጃ መውሰዱን ትቀጥልበታለች" ብለዋል። 

የእገዳ እርምጃውን አስመልክቶ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽ የዋሽንግተን እርምጃ "ፍፁም መሠረተ ቢስ የሆነ ውንጀላ ነው፤ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር በእርግጥም ለሐሰት ክሶቹ ማስረጃ አለኝ የሚል ከሆነ ጉዳዩን ለገለልተኛ ዳኝነት እንዲያቀርብ ኤርትራ ጥሪ ታቀርባለች" ብሏል።     

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now