ተመድ ለትግራይ መርጃ $35 ሚሊየን ለገሰ

*** እርዳታው አገር ውስጥ ለተፈናቀሉና ሱዳን ለተሰደዱ ኢትዮጵያውያን መደጎሚያነት ዋይ ነው

UN aid package

Ethiopian Asafu Alamaya, a 80-year-old blind who fled the Tigray conflict, sits in her makeshift shelter at the Um Raquba refugee camp in Sudan Source: Getty

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በፌዴራል መንግሥቱና በሕወሓት መካከል በተፈጠረው ሶስት ሳምንታትን ያስቆጠረ ግጭት ሳቢያ በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉና የሱዳንን ድንበር ተሻግረው ለስደት ለተዳረጉ ኢትዮጵያውያን መርጃ እንዲውል $35.6 ሚሊየን መቸሩን በዲሴምበር 17 መግለጫው አስታወቀ።

የ$13 ሚሊየን ችሮታው ወጪ የተደረገው ከተመድ ማዕከላዊ የአስቸኳይ ግብረ ምላሽ ድጎማ ሲሆን የሚውለውም ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈናቀሉ ዜጎች ሲሆን፤ ተጨማሪ $5 ሚሊየን ሱዳን በቅርቡ በስደተኛነት ለገቡቱ መርጃ ይውላል። በታካይነትም $12 ሚሊየን ከኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ ድጎማና $5.6 ከሱዳን የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ ድጎማ ወጪ ሆኗል።

በእርዳታ ክፍፍሉም ወቅት ለሴቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋውያንና የግብረ አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተመድ ገልጧል።

የመንግስታቱ ድርጅት አያይዞም "እንዲህ ያሉ ግጭቶች አንዴ ከቁጥጥር ውጪ ከሆኑ ለማስቆም በእጅጉ አዋኪ ነው። የተቀጠፉ ሕይወቶች አይመለሱም፤ ዘላቂ ዕርሮዎችንም ይፈጥራሉ። በአሁኑ ወቅት ሕጻናት ከእርዳታ ተገልለዋል። ያልተገደበ ተደራሽነት እንዲኖረን እንሻለን" ብሏል።  

 

 


1 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now