ቪክቶርያ ባለፉት 24 ሰአታት 12 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦችን ቁጥር ያስመዘገበች ሲሆን ከአረጋውያን መጦሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘም ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በለፉት 14 ቀናት በተሰበሰቡት መረጃዎች መሰረት የተያዦች ቁጥር በተከታታይ መቀነስን አሳይቷል ፡፡
ቁጥሮቹም ከ 30 እስክ 50 ባሉት ውስጥ በመሆናቸውም ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የተጣሉ ገደቦችን ለማላላት እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡
የቪክቶርያው ፕሪምየር ዳንኤል አንድሪውስ በተቀመጠው ፍኖተ ካርታ መሰረት ቪክቶርያ ወደ ደረጃ 2 ለመሸጋገር በጥሩ መስመር ላይ ነች ብለዋል ፡፡
አያይዘውም “ በመጪው እሁድ ከፍተኛ የሚባል እርምጃ የምንወስድበት ላይሆን ይችላል ፤ ፍኖተ ካርታውም ይህንን አይፈቅድም ነገር ግን ቀስ በቀስ ጥንቃቄን እና ተከታታይነትን በተሞላ መልኩ ነው እንዲከናወን የምንፈልገው ፤ ምክንያቱም መቀነሱም የታየው ቀስ በቀስ እና ተከታታይ በሆነ መልኩ ነው ብለዋል፡፡ ’’
Share

