ቪክቶሪያ 484 አዲስ የኮሮናቫይረስ ሬኮርድ አስመዘገበች

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ኮሮናቫይረስ መጠን ወደ ሁለት ዲጂት አደገ

most Victorians are failing to self-isolate when they show coronavirus symptoms

Victorian Premier Daniel Andrews. Source: AAP

ቪክቶሪያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 484 አዲስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ስታመዘግብ፤ ሁለት ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ሁለቱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች በአረጋዊያን መጦሪያ የነበሩና በ90ዎቹ ዕድሜ ያሉ ናቸው።

ይህም ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈውን ሰዎች ቁጥር 44 አድርሶታል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የተከሰተው 484 የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በአውስትራሊያ ውስጥ የመጀመሪያው ከፍተኛ መጠን ነው። 

ቀደም ሲል በአገር አቀፍ ደረጃ ማርች 28 በአንድ ቀን አዲስ ተመዝግቦ የነበረው የቫይረሱ ከፍተኛ መጠን 469 ነበር።  

ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 53 ፐርሰንቱ ራሳቸውን አግልለው ባለመቆየታቸው ቅር መሰኘታቸውን ሲገልጡ፤

"ከጁላይ 7 እስከ ጁላይ 21 ባሉት ጊዜያት 3810 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ራሳቸውን አልገለሉም። ከ3400 በቫይረሱ ከተያዙቱ ምርመራ እስካደረጉ ድረስ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ከአሥር ዘጠኙ ራሳቸውን አለማግለላቸውን ሪፖርት ሳደርግ በጣም፣ በጣም ደስተኛ አይደለሁም። በጣም አዝኛለሁ" 

"ምርመራዎችን እስከሚያካሂዱ ድረስ ቤት ውስጥ ካልተቆየ በስተቀር ቁጥሮቹ ወደ ታች አይወርዱም። ከቶውንም እያሻቀቡ ይሄዳሉ እንጂ። የስድስት ሳምንታቱ ገደብም ለስድስት ሳምንታት ብቻ አይሆንም። ከዚያ በላይ ሊቀጥል ይችላል" ብለዋል።     

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 16 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። 

በቫይረሱ ከተጠቁት ውስጥ አንዱ ሆቴል ውስጥ ወሸባ ገብተው ካሉት ሲሆን፤ የተቀሩት 15ቱ በማኅበረሰብ ተጋቦት የተያዙ ናቸው።

 

 

 

 

 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now