የአገሪቱ ቀደምት ነዋሪዎች በተለያዩ የበአላት ቀናት የተጨናነቀው የቪክቶሪያ የቀን መቁጠሪያ የናይዶክ ሳምንትንም ይፋው የእረፍት ቀን አድርጎ እንዲያካትት ጥሪ አቅርበዋል ።
የ 2022 የናይዶክ ሳምንት ሊጠናቀቅ ሲቃረብ የተመረጡት የቀደምት ነዋሪዎች ‘አሰባሳቢ በቪክቶሪያ ፤ የናይዶክ ሳምንት የእረፍት ቀን እንዲሆን የሚጠይቅ ፊርማ ማሰባሰብን ጀምረዋል ።
“ ለፈረስ ውድድር ቀን ፤ ለተወረርንበት ቀን ፤ ለፉቲ ግጥሚያዎች ፤ ለጦርነቶሽ እና በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ንግስት የተሰየሙ የእረፍት ቀናት አሉ ። ነገር ግን የአገሪቱ ቀደምት ነዋሪዎች ታሪካችንን እና ባህላችንን የምናካፍልበት የተለየ የእረፍት ቀን የለንም ።” ይላል በኦን ላይን የተዘጋጀው የፊርማ ማሰባሰቢ።
የናይዶክ ቀን የእረፍት ቀን የመሆኑም ፋይዳ ፤ ማህበረሰቡ በጋራ በመሆን የተሻለ ነገን ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ይጠቅማል ሲሉ የህብረቱ ተባባሪ መሪ ማርከስ ስቲወርት ተናግረዋል።
የናይዶክ ሳምንት አጀማመሩ በ1920 አካባቢ የነበረ ሲሆን መነሻ ሃሰቡም የቀደምት ነዋሪዎች እና የቶርስ ስትሬት ወሽመጥ አውስትራሊያውያንን የኑሮ ሁኔታን እና አያያዝ አስመልክቶ ግንዛቤን ለማስጨበጥ በሚል መርህ ነው ።
“ በምናባችሁ ተመልከቱ ከናይዶክ ሳምንት አንዱ ቀን የናይዶክ የእረፍት ቀን ቢሆን በእርግጥም እውነተኛ የሆነውን አላማ ያሳያል። ” ሲሉ የተናገሩት የኒራ ኢሊም ቡሉክ የሆኑት ሰው ናቸው ።
ባለፈው አርብ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማእከላዊ ሜልበርን የናይዶክ ልዩ ልዩ ትእይንቶችን ለማሳየትም በአደባባይ እንደወጡም ይታወሳል ።