ቪዛዎች ለባሕር ማዶ ተማሪዎች

አውስትራሊያ ሙሉ ሕይወትንና ግለትን የተላበሰ ባሕላዊ ዝንቅነቷ፣ ቀለል ያለ የአኗኗር ዘዬዋና ያልተነካ ተፈጥሯዊ ውበቷ ተዘውትሮ የምትነሳባቸው መለያዎቿ ናቸው። በጣሙን ጠቀም ያለ ድጎማ የሚያገኙ ቤተ መጽሕፍቶቿና ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ የምርምር ተቋማቶችዋም የዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ቀልብ በመዳረሻነት ማራኪ ናቸው።

overseas students

Source: Getty Images

አንኳሮች


  • የጋራ ብልፅግና የምዝገባ መካነ ጥናቶችና ለባሕር ማዶ ተማሪ ኮርሶች (CRICOS) ድረገጽ የሁሉንም የትምህርት ተቋማትን ዝርዝሮችና ለዓለም አቀፍ ተማሪዎች ዝግጁ የሆኑ የትምህርት ዓይነቶችን መረጃ ይሰጣል።
  • የተማሪ ቪዛ (Subclass 500) ያላቸው ተማሪዎች በ14 ቀናት ውስጥ እስከ 40 ሰዓታት መሥራት ይችላሉ
  • ጥናታቸውን ከጨረሱ በኋላ ለጊዜያዊ የምሩቃን ቪዛ  (Subclass 485) ማመልከት አሊያም ዕውቅና ላለው የምሩቃን ቪዛ (subclass 476) ማመልከት ይችላሉ

ከመምጣትዎ በፊት

ዓለም አቀፍ ተማሪ ሆነው አውስትራሊያ ውስጥ መማር የሚሹ ከሆነ፤ የተማሪ ቪዛ (Subclass 500 ተብሎ የሚታወቀውን) ሊያገኙ ይገባል።

መመዘኛውን ለማሟላት በጋራ ብልፅግናው የምዝገባ መካነ ጥናቶችና ለባሕር ማዶ ተማሪ ኮርሶች (CRICOS) የሙሉ ጊዜ ተማሪነት ተቀባይነትን ማግኘት ይኖርብዎታል።

በሆልዲንግ ሬድሊች - የሕግ ስፔሽያሊስትና የመጤ ወኪል የሆኑት ማሪያ ጆክል፤ ለተማሪ ቪዛ ከማመልከትዎ በፊት ሕጋዊ ምዝገባ ካለው የትምህርት ሰጪ ተቋም የምዝገባ ማረጋገጫ ሊኖርዎት እንደሚገባ ይናገራሉ።
በአውስትራሊያ የጋራ ብልፅግና የትኞቹ የትምህርት ዓይነቶች ተመዝግበው እንዳሉ ለማወቅ የ (CRICOS) ድረገጽን መጎብኘት ይችላሉ።
ከምዝገባው ጎን ለጎንም የገንዘብ፣ የጤናና የባሕርይ መመዘኛዎችን ማሟላት፣ የግል የጤና ኢንሹራንስ ሊኖርዎትና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ፈተናን ማለፍም ይገባዎታል።

የቪዛ ማመልከቻ ዋጋ ከ$620 ይጀምራል። በየዓመቱ የሚሰጡ ቪዛዎች ላይ ገደብ የለም።
campus, university student, different heritages and backgrounds
A small group of Australian university students from different heritages and backgrounds. Source: Getty Images
አውስትራሊያ ውስጥ 

አውስትራሊያ ውስጥ እየተማሩ ሳለ በተርም፣ በሙሉ የትምህርትና ዕረፍት ጊዜያት መካከል እስከ 40 ሰዓታት በየአሥራ አራት ቀናቱ መሥራት ይችላሉ።

የተማሪ ቪዛዎ - ትምህርትዎን እስኪጨርሱ ድረስ ከእርስዎ ጋር አውስትራሊያ ውስጥ የሚቆይ አንድ የቤተስብዎን አባል በቪዛ ማመልከቻዎ ላይ እንዲያሠፍሩ ይፈቅድልዎታል። 
የተማሪ ቪዛው በቀዳሚነት ትምህርታቸውን እንዲማሩ እንጂ እንዲሠሩ ስላልሆነ፤ በትምህርታቸው ላይ ማተኮርን ግድ ይላል።
university lab, female medical students, Chinese ethnicity, Middle Eastern ethnicity
Two female medical students Chinese and Middle Eastern ethnicity respectably, studying anatomy in university lab using an anatomical model. Source: Getty Images
የትምህርት ቪዛዎን የቆይታ ጊዜ የሚወስነው የሚያጠኑት የትምህርት ዓይነት ነው። እስከ አምስት ዓመታት ያህል ሊረዝም ይችላል።

ማሪያ ጆክል - የቪዛ ፈቃድ ማረጋገጫ ደብዳቤንና የቪዛ መስፈርቶችን በውል ማንበብ ጠቃሚ መሆኑን ያሳስባሉ።

የኢሚግሬሽን ዲፓርትመንት የትምህርት ቪዛው ደንብ ተጥሶ ከተገኘ ሊሰርዝ  እንደሚችልም ጠቁመዋል።
ብዙውን ጊዜ ሰዎች የቪዛ ማብቂያ ጊዜያትን ልብ ብለው አይመለከቱም።
Visas for overseas students
Outside the Australian campus, graduate students, wearing graduation gown and cap, happy and embracing. Source: Getty Images

ትምህርትዎን ሲያጠናቅቁ

የተማሪ ቪዛ ከምረቃ ቀንዎ ቀደም ብሎ ጊዜው ሊያበቃ ይችላል። ያ ዓይነት ሁኔታ በሚገጥምዎ ወቅት የጎብኚ ቪዛ (Subclass 600) ለማመልከት መሥፈርቱን ያሟላሉ።

ትምህርትዎን በሚያጠናቅቁበት ወቅት ትንሽ መቆየት ከፈለጉ ጊዜያዊ የምሩቅ ቪዛ (Subclass 485) ወይም ዕውቅና ያለው ምሩቅ ቪዛ (subclass 476) ሊያመለክቱ ይችላሉ።

ጊዜያዊ የምሩቅ ቪዛ (Subclass 485) ሁለት ምንጮች አሉት – የምሩቅ ሥራና የድኅረ - ጥናት ሥራ።

 የምሩቅ ሥራ ምንጭ ተማሪዎች እስከ 18 ወራት ያህል እየሠሩ እንዲማሩ ይፈቅዳል።

የድኅረ - ጥናት ምንጭ አመልካቾች አውስትራሊያ ውስጥ ከሁለት እስከ አራት ዓመታት እንዲሠሩ ያስችላል።

ዕውቅና ያለው ክህሎት ምሩቅ ቪዛ (subclass 476) የተቀረጸው በተለይ ይህ ነው ከሚባል ተቋም የዲግሪ ወይም ከፍ ያለ ስልጠና ለወሰዱ የምሕንድስና ተማሪዎች ነው።

ለተጨማሪ መረጃ የ Department of Immigration and Border Protection ወይም የ CRICOS website ድረገጾችን ይጎብኙ።

 


Share

Published

Updated

By Josipa Kosanovic
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service