እንኳን በሰላም ወደ አገራችን መጣችሁ ማለት ምን ማለት ነው ?

በተለያዩ የህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ በአቦርጅናል ልማዳዊ ባለቤቶች ስነስርአቶችን ሲደረግ ማየት እየጨመረ መጥቷል ። ይህ የእንኳን ደህና መጣችሁ መንፈሳዊ ስነስርአት “ እንኳን በሰላም ወደ አገራችን መጣችሁ ” ይባላል

Welcome Commonwealth Games

Source: Ian Hitchcock/Getty Images

አንኳሮች

  • ወደ አገራችን እንኳን በሰላም መጣችሁ የሚለው ስነስርአት እና ለአገሪቱ እውቅናን ለመስጠት የሚደረገው የተለያየ ነው።
  • እንኳን በሰላም ወደ አገራችን መጣችሁ የሚለውን የሚፈጽሙት ከተወሰነ ስፍራ የመጡ የአገሪቱ ልማዳዊ ባለቤቶች ብቻ ናቸው።
  • በራስዎ ድምጽ እውቅናን መስጠትን  እንዲችሉ የተዘጋጁ የተለያዪ መረጃዎች 
ወደ አገራችን እንኳን በሰላም መጣችሁ የሚለው መልእክት ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊት በንግግር ፤ በጭፈራ ወይም ጭስን በማጨስ ስነስርአት ሊከናወን ይችላል ። የእንኳን በሰላም መጣችሁ ስነስርአት የሚከናወነውም በአገሪቱ ልማዳዊ ባለቤቶች፤ ሁነቱ በሚከናወንበት ስፍራ ነው ።

እንኳን በሰላም መጣችህ ማለት ምን ማለት ነው ?

እንኳን በሰላም ወደ አገራችን መጣችሁ ማለት ፤ መንፈሳዊ ደህንነትን ማረጋገጥ ማለት ነው የሚሉት በካንብራ ክልል የንጉናዋል አረጋዊ የሆኑት ጁድ ባርሎው ናቸው ።

“ እንኳን በሰላም መጣችሁ ማለት ከቅድመ አያቶቻችን መንፈስ ጋር በመነጋገር እነዚህ ሰዎች ወደአገራችን እንዲገቡ ይፈቀድላቸው ማለት ነው። ለዚህች አገር ክፉ ነገርን እንደማያደርጉ እናምናለን ስለሆነም አትጉዷቸው ማለት ነው ” ይላሉ ።

“ እኔ ወደ ሌሎች ቀደምት ህዝቦች አገር ስሄድ ፤ እንኳን ደህና መጣሽ የሚለው ስርአት እንዲደረግልኝ እጠብቃለሁ፤ በዚህም እኔ እዚያ በመገኘቴ መንፈሳቸው መስማማቱን ማወቅ ይኖርብኛል፤ ምክንያቱም አሁንም ድረስ ከእኛ ጋር ናቸው - እነሱ በእንስሳቱ እና ዛፎቹ ውስጥ አሉ ። ”

አገር ምንድን ነው ?

“ አገር ” የሚለው ቃል የወሰኑ እና የተወሳስቡ ሀሳቦችን የሚወክል ነው። መሬትን ፤ የውሀ መተላለፊያዎችን እና ሰማይን የሚወክል ነው ፤ ግን ደግሞ የህይወትን እና ቤተሰብን ትስስር ሀሳብ በውስጡ የያ ነው ይላሉ ጁድ ባርሎው ።

“ በአገሪቱ ላይ ስኖር የሚሰማኝ ሀይል አለ ፤ እዛ በማልኖር ጊዜ አንድ ነገር ከህይወቴ እንደጠፋ ይሰማኛል ።  በተጨማሪም ከአያት ቅድመ አያቶቼ ጋር የሚያገናኘኝ ነው ፤ ምክንያቱም የአቦርጂናል ህዝብ የቃል ታሪክ ያላቸው ሲሆን እነዚህን ታሪኮች አቅፋ የያዘችውም አገሪቱ ናትና ።”

ማንኛውም ሰው  ወደ አገራችን እንኳን  በሰላም መጣችሁ ማለት ይችላልን ?

ወደ አገራችን እንኳን በሰላም መጣችሁ ማለት የሚችሉት እርስዎ በተገኙበት ስፍራ ያሉት የአገሪቱ ልማዳዊ ባለቤቶች ብቻ ናቸው ።
Welcome Big Bash
Welcome to Country performed at Big Bash League, Perth Source: Paul Kane/Getty Images
በአብዛኛውም ለአንድ የተለየ አካባቢ በይፋ እውቅና የተሰጣቸው ልማዳዊ ባለቤቶቹ ናቸው የሚሉን ፖል ፓቶን ናቸው ። እሳቸውም የጉናይ እና ማኖራ ሰው ሲሆኑ የደቡብ ምስራቅ አውስትራሊያ የቪክቶሪያ ፌዴሬሽን  ባህላዊ ባለቤቶች ኮርፖሬሽን መሪ ናቸው  ።

“ ልማዳዊ ባለቤቶች ከተለየ ቦታ ወይም አገር ጋር ትስስር አላቸው ፤ ሁላችንም ለዚያ ለተለየ ቦታ ወይም ባህላዊ ስፍራ እና በሺዎች ከሚቆጠሩ ትውልዶች ጋር ጸንቶ ለቆየውን ትስስር ከበሬታን መስጠት በጣም አስፈላጊ ነው። ” ብለዋል

በተወሰኑት የአውስትራሊያ ግዛቶች ባህላዊ ባለቤቶች በጉልህ የሚታወቁ ሲሆን ፤በአንጻሩም በይፋ እውቅናን ያልተሰጣቸው ባህላዊ ባለቤቶችን ፤ ለመለየት የተወሰነ ምርመር ማድረግ ግድ ይላል ።

የመንግስት ድርጅቶች እና የአካባቢ ቀበሌዎች ከልማዳዊ ባለቤቶች ጋር ሊያገናኝዎት ይችላሉ ። በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የአቦርጅናል መሬት ካውንስል ወይም የአቦርጅናል የጤና ድርጅት እንዲሁ  ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲያመሩ አቅጣጫን ያመላክትዎታል ።
Welcome Super Netball
Welcome to Country performed before Super Netball, Melbourne 2022 Source: AAP Image/James Ross
ለአገሪቱ “ እውቅናን መስጠት ” የተለየ ነውን?

ለአገሪቱ እውቅናን የመስጠት ስርአት አንድ ስብሰባ ወይም የተለይ ዝግጅት ከመጀመሩ በፊት የሚደረግ የአክብሮት ስነስርአት ነው ።ልዪነቱም ይህ ስነስርአት በአገሪቱ ልማዳዊ ባለቤቶች አማካኝነት የሚደረግ አለመሆኑ ነው።

“ ለአገሪቱ እውቅናን መስጠት ሁላችንም ልናደርገው እንችላለን ፤ ጥቁር ወይም ነጭ ከየትም ብንመጣ፣ ” ያሉት የኤስ ቢ ኤስ የነባር ዜጎች  ሽማግሌ የሆኑት ርሆንዳ ሮበርትስ ናቸው።

“ስለዚህ እውቅናን መስጠት ማለት ስራዎትን እየሰሩበት ወይም እየኖሩበት ያለው ስፍራ እርስዎ የመጡበት ስፍራ አይደለም ማለት ነው ፤ ባይሆንም ምንም ማለት አይደለም ። ምክንያቱም እዚያ መኖርን ይችላሉ ፤ ለልማዳዊ ባለቤቶችም  እውቅናን መስጠት ይችላሉ። ”

የእውቅናን ስነስርአትን ማዘጋጀት

የእውቅና ስነስርአትን በተመለከት የተወሰነ ቃል የለም ፤ ቁልፍ መርሆቹ በጽኑ መነሳሳት እና ከልብ የሆነ ፍላጎት ናቸው ። ስለሆነም ተዘጋጅቶ የተቀመጡ አባባሎችን ከመናገር ይልቅ ከልብ አፍልቆ ለመናገር የሚያስችልን እድልን ይፈጥራል ።

የእውቅናን ስነስርአትን ለማዘጋጀት እንዲረዳዎት በኦንላይን ላይ የተቀመጡ መረጃዎች አሉ።

“ ይህንን በመጨረሻ ሰአት ላይ በጥድፊያ አያድርጉት ፤ የአጠቃልይ ዝግጅቱ አካል እንደመሆኑ መጠን በደንብ ያቅዱ ” የሚሉት ጁድ ባርሎው ናቸው ።

“ ይህ የአክብሮት ምልክት ነው ”
Acknowledgement fashion show
Acknowledgement of Country given by Aunty Yvonne Weldon during the First Nations Fashion + Design show, Sydney 2022 Source: Stefan Gosatti/Getty Images
የምትገናኙበትን ቦታ አገር እና ስም በተመለከት የተለየ ትኩረት ይስጡ ።

የልማዳዊ ባለቤቶቹ  በይፋ እውቅና ከተሰጣቸው ፤ ስማቸውን ይጥሩ ፤እንዲሁም ለቀደምት አረጋውያን ለአሁን እና ወደፊት ለሚመጡት ከበሬታን ይስጡ ።

የልማዳዊ ባላቤቶቹ በግልጽ የማይታወቁ ወይም በርካታ ቡድኖች ከሆኑ እና  ፤ ለአንድ የተወሰነ የአገሪቱ ክፍል ፍላጎትን ካሳዩ‘ ለልማዳዊ ባለቤቶች ’እውቅናን መስጠት ብልህነት ነው፤ ሲሉ ፖል ፓቶን ተናግረዋል ።


Share

Published

Updated

By Melissa Compagnoni
Presented by Martha Tsegaw

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
እንኳን በሰላም ወደ አገራችን መጣችሁ ማለት ምን ማለት ነው ? | SBS Amharic