አንኳሮች
- የዓለም አቀፍ ብዙኅን መገናኛ የዜና ወኪሎች አገርኛና ዓለም አቀፍ ሙያዊ አተያዮች
- የዓባይ ወንዝና ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ፕሮጄክት
- የሚዲያ ሙያዊ ክህሎት ምዘና
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ግዘፍ እየነሳ ከመጣ ወዲህ በኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን መካከል የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲና ሕዝብ ግንኙነት አየር ወበቅ የተመላው ሆኗል።
የመልዕክቶቻቸው ስልና ሙርድነት ግና እንደሚጠቀሙባቸው የብዙኃን መገናኛ፣ የመንግሥታቱ አጀንዳ ቀራጭነት አቅምና የብዕር ዘንገኞቻቸው የቀለም ጠብታዎች ሚዛኑ ከፍና ዝቅ ይላል።
ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞቹ የአገራቱን የሕዳሴ ግድብ የሚዲያ አዘጋገቦች ይመዝናሉ።