ኮቪድ - 19 የምርጫ ደንቃራ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ሥልጣን ክፍተት ወይም ሕገ መንግሥታዊ ቀውስ ይፈጥር ይሆን?

Source: Courtesy of FBC
በኮሮናቫይረስ ሳቢያ አገር አቀፍ ምርጫ ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፣ ሕገ መንግሥትን ማሻሻልና የሕገ መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሚሉ አራት የመፍትሔ አማራጮችን አቀረቦ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ያካተተ ክርክር ተካሂዶባቸዋል። የተለያዩ አተያዮች ተስተጋብተዋል። አገርኛ ታዛቢዎችም ጥቂቶች አጋጣሚውን ለአቋራጭ የስልጣን መቆናጠጫነት ሲከጅሉ፤ ሌሎች አገርን በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረት ላይ ለመገንባት ኢትዮጵያን ከገጠማት ፖለቲካዊ ፈተና ለማውጣት የሚበጅ ብልሃት ለማፈላለግ ጭንቀትና ጥበት ሲሰማቸው ማስተዋላቸውን አንጸባርቀዋል። የ ’አገር እንዴት ሰነበትች?’ ዝግጅታችን ሁነኛ ምልከታ አለው።
Share