አመታዊው የናይዶክ ሳምንት ሽልማት በናርም (ሜልበርን) የተከናወነ ሲሆን በመግቢያውንም አክስት ጆይ እንኳን ወደ አገራችን በሰላም መጣችህ የሚለውን ስነስርአት አከናውነዋል ።
“ ውብ ከሆነው የባህርዛፍ ጫፍ እስክ መሬት ስር ፤ ከእኛ ጋር ስትቀላቀሉ ፤ ለእኛ የሚያሳየን ነገር የቆምንበትን ይህንን ቀደምት መሬት ላበለት ቅድመ አያቶቻችንን መንፈስ ከበሬታን መስጠታችሁን ነው ። “
የኢንዲጅነስ ሚኒስትር ሊንዳ በርኒ በበኩላቸው በፌደራል መንግስት እና ቀደምት ነዋሪዎች መከከል ስምምነት እንደሚፈጸም ተናግረዋል ።
" ሁላችንም ይህችን አገር መቀየር ይኖርብናል ፤ ይህችን አገር እንቀይራለን፤ ምክንያቱም ቀኑ መጥቷልና።"
የናይዶክ ሳምንት ተሸላሚ ከሆኑት መካከል አጎት ጃክ ቻርልስ፤ የጠፉት ትውልዶች ተብለው ለሚታወቁት ቀሪ ዜጎች ላበረከቱት አስተዋጥጸኦ ፤ የአረጋዊ ወንድ ሽልማትንን ወስደዋል።
የቀድሞዋ ቴኒስ ተጫዋች አሽ ባርቲ የአመቱ ሰው በመባል የተሰየመች ሲሆን ፤ የ26 አመቷ አሽ ባርቲ ከአገር ውጭ በመሆኗም ሽልማቷን አባቷ በእሷ ስም ተቀብለዋል ።
ከዚህ በተጨማሪም የአውስትራሊያ ፉትቦል የሲድኒ ስዋን ተጫዋች የሆነው ጃክ ቻርልስ፤ የስፖርት ሰው ሽልማትን ተቀብሏል ።
ናይዶክ ሳምንት እስክ ጁላይ 10 ደርስ ይቀጥላል ። (የጀመረው በጁላይ 3 ነው )