ወ/ሮ ነፃነት ኃይሌ እና አቶ ቶም ኑናን፤ የ New Flower Sound 2019 የኢዮሃ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት አስተባባሪዎች፤ ዓርብ መስከረም 1 ቀን / September 11 በ 342 High St, Northcote ከ 6:00 pm እስከ 11:00 pm ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ታዳሚዎች ስላዘጋጁት ልዩ ኩነት ያስረዳሉ። የኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና አውስትራሊያውያን ማኅበረሰብ አባላት የአዲስ ዓመት ታዳሚ እንዲሆኑ ያጋብዛሉ።
አንኳሮች
- የአዲስ አበባ ድምፅ ምሥረታ
- የአዲስ ዓመት ቅበላ
- ዝርዝር ፕሮግራም
ይህ ፕሮጀክት ለእኔና ለነፃነት በጣም ትርጉም ያለው ነው። ከኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ጋር አብረን በመሥራት አንድ ልዩ ነገር ማድረግ እንፈልግ ነበር። እናም፤ ይህንን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ የድምፅ ሲስተም ጋር ማክበሩ በጣም ደስ ያሰኘናል።ቶም ኑናን

Share






