Facing Justice: Eshetu Alemu

Source: Courtesy of Public, KA, KM, and SA
የቀድሞው የደርግ አባልና የጎጃም ክፍለ ሃገር ተጠሪ የነበሩት እሸቱ ዓለሙ ወጣቶችን አለአግባብ ለእሥራትና ለስቃይ ዳርገዋል፣ ሲልም ለሕልፈተ ሕይወት አብቅተዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ዘ-ሄግ ኔዘርላንድስ ውስጥ ክሳቸው በአንድ ፍርድ ቤት እየታየ ነው። ብይኑም በወርኃ ዲሴምበር አጋማሽ ላይ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል። ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ የክሱን አነሳስና ምስረታ ሂደት አስመልክቶ፣ ከሰለባዎቹ አንዱ የሆኑት አቶ ቁምላቸው መኩሪያ በእሳቸውና በጓደኞቻችቸው ላይ በወቅቱ ስለደረሱት እሥራት፣ ግርፋትና ግድያዎችን በተመለከተ ጉዳዩን ለያዙት የኔዘርላንድስ የሕግ ባለሙያዎች ከሰጡት የምስከር ቃል አጣቅሰው፤ እንዲሁም የፍርዱን ሂደት በቅርበት ያላማቋረጥ የተከታተሉት አቶ ሲራክ አሰፋው በዓቃቤ ሕግ፣ በተከሳሽና የመከላከያ ጠበቆች አማካይነት የቀረቡ ማስረጃዎችንና ክርክሮችን ነቅሰው ይናገራሉ።
Share




