ውልደታቸው ሰንዳፋ፤ ኢትዮጵያ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ፊደል የቆጠሩት እንደ አያሌ ኢትዮጵያውያውያን ቄስ ትምህርት ገብተው ሳይሆን በቀጥታ አስኳላ ዘልቀው ነው።
በቀለሙ ገፍተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል። ኮሌጅ በጥሰዋል። በዚያም አልተገቱም፤ ለድኅረ ዶክትሬት ኮሎራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲን ረግጠው እ.ኤ.አ. በ1975 በእንሰሳት ሕክምና ተጠብበዋል።
Solving Immune deficiency 1976 Source: Courtesy of AM
Advertisement
በምርምር ግኝታቸው የመድኅን ማነስን (immune deficiency) ለመክላት በመብቃታቸው በሚሊየን የሚቆጥሩ የእንሰሳት ህይወቶችን ታድገዋል። በቢሊየን ዶላርስ የሚቆጠሩ ወጪዎችን አድነዋል።
Source: Courtesy of AM
በኤች.አይ.ቪ ኤይድስ ምርምር መስክ ከዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶች ጋር ተሰማርተው መከላከያውን ለማግኘት ብርቱ ጥረቶችን አከናውነዋል።
ጥሬ ሥጋ መመገብን ልማዳቸው ላደረጉቱና በዓል በመጣ ቁጥር በድብቅ በየእርሻ ማሳው ዘልቀው ሙክትና ድልብ ሰንጋ ለሚያሳርዱቱ፤ ከጤናና ከሕግ አኳያ ምክረ ኃሳቦቻቸውን ያጋራሉ።
“ጥሬ ሥጋ መብላት እንደ ቁማር ነው፤ ሁሌም አያዋጣም። ኃይለኛ በሽታ የተገኘ ቀን ብዙ ሰው ሊያልቅ ይችላል።” - ዶ/ር አበራ ሞላ Image “ብዙዎች ኢትዮጵያውያን በየእርሻው እየሔዱ ያንን በግ፤ ያንን ከብት እረድልኝ ሲሉ ከሸጠላቸው ሰው ኃላፊነቱን መውሰዳቸውን አይረዱም። ያን ሥጋ ሰው በልቶ ቢሞት፤ ኃላፊነቱ ያሳረደው ወይም የገዛው ሰው ነው።” - ዶ/ር አበራ ሞላ