Life and Legacy: Dr Aberra Molla - Pt 2

 Life and Legacy: Dr Aberra Molla - Pt 2

Dr Aberra Molla Source: Courtesy of AM

ዶ/ር አበራ ሞላ በማጠቃለያ ክፍል ሁለት ዝግጅታችን የግዕዝ ፊደልን እንደምን በዘመነኛው ኮምፒዩተር ለትየባ እንዳበቁ፤ በዘረፋ የተወሰደውን የአክሱም ሐውልት ከሮም አስነቅሎ ወደ እናት ምድሩ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ስላበረከቱት አስተዋጽዖና በቅርቡ የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማኅበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ስላበረከተላቸው ሽልማት ያነሳሉ።


ዶ/ር አበራ ሞላ በክፍል አንድ ግለ ሕይወት ትረካቸው፤ ከትውልድ ቀዬአቸው ሰንዳፋ አንስተው ወደ አገረ አሚሪካ አሻግረው አጓጉዘውናል።

እዚያም በኮሎራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ድኅረ-ዱክትርናቸውን አጠናቅቀው፤ በተጠበቡበት የእንሰሳት ሕክምናው የምርምር መስክ የመድኅን ማነስን (immune deficiency) ማስወገድ በመቻላቸው የበርካታ ሚሊየን እንሰሳት ሕይወቶች መታደጋቸውን፤ በኤች.አይ.ቪ ኤይድስ የምርምር ዘርፍም ከዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶች ጋር ለበሽታው መቋቋሚያ ለመፍጠር ያደረጓቸውን አስተዋጽዖዎች አውግተዋል።

ሲልም፤ ጥሬ ሥጋን መብላት ባሕላዊ የአመጋገብ ልማዳቸው ያደረጉ ኢትዮጵያውያን በተለይም በዓላት በመጡ ቁጥር ወደ እየርሻው እየዘለቁ ሙክትና ሰንጋ ማስጣል ለሚያስከትሏቸው ጠንቆች የተጠያቂነት ኃላፊነትን እንደሚያስወስዳችው፤ እንዲሁም፤ ጥሬ ሥጋ የመብላቱን ነገር ከቁማር ጨዋታ ዕጣ ፈንታ ጋር አያይዘው የሚያስከትሏቸውን የጤናና የሕግ መዘዞችን አክለው የንፅፅሮሽ ምክረ ሐሳባቸውን ቸረዋል።

የክፍል ሁለት የትኩረት አቅጣጫቸው ከብዙ ድካም በኋላ ኢትዮጵያውያን የግዕዝ ፊደልን በኮምፒዩተር መጠቀም እንዲችሉ በማድረጋቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐሴት ገልጠዋል።
 Life and Legacy: Dr Aberra Molla - Pt 2
GeezEdit iPhone App Source: Courtesy of AM
ፊደላችን ድምጻዊ ፊደል ስለሆነ አዳብረነው ወደፊት ለሌላው ዓለም ለማስተዋወቅ ይዘነው የምንሔደው ነው ባይ ናቸው።
 Life and Legacy: Dr Aberra Molla - Pt 2
Amharic Alphabet Source: Courtesy of AM
በሌላም በኩል፤ የግዕዝ ፊደልን በላቲን የመተካቱ እርምጃ ሳይንሳዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ነው ብለው ይከራከራሉ። ሙያዊ ምክረ ሐሳባቸውንም ያጋራሉ።
“የግዕዝ ፊደላችን የኦሮምኛ ቋንቋን መተየብ አይችልም ተብሎ ወደ ላቲን መሔድ ስሕተት ነው። እንዲያውም የኦሮምኛ ቋንቋችን እንዳይዳከም፤ ኦሮሚፋን ተጨማሪ የአገሪቱ የሥራ ቋንቋ ብናደርግ የተሻለ ይመስለኛል።” - ዶ/ር አበራ ሞላ
ዶ/ር አበራ፤ በጣሊያን ወረራ ወቅት ተዘርፎ የሮማን ፒያሳ ማድመቂያ የነበረው የአክሱም ሐውልት ለአገሩ ምድር በቅቶ የኢትዮጵያን  ቀደምት የሥልጣኔ አሻራን እንዲያጎላና ታሪካዊ ሥፍራውን እንዲያገኝ  ብርቱ ሚና ተጫውተዋል።
 Life and Legacy: Dr Aberra Molla - Pt 2
Axum obelisk Source: Courtesy of AM



Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service