Watch FIFA World Cup 2026™ LIVE, FREE and EXCLUSIVE

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 2

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 2

Emeritus Prof Bereket Habte Selassie Source: Courtesy of Elias

ፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ፤ በክፍል ሁለት የግለ ሕይወት ትረካቸው የዓይን ምስክርና ተሳታፊ የነበሩባቸውን ሁለት አንኳር የታሪክ ምዕራፎችን ያነሳሉ። የ1953ቱን የታህሳስ ‘ግርግር’ እና የየካቲት ‘66ቱን የአብዮት ‘ፍንዳታ’ ታሪካዊ ክስተቶች።


በታህሳሱ ግርግር ወቅት በአብዮት ቀስቃሽነትና መሪነት ለክስ የተዳረጉትን በዳኝነት ተሰይመው እንዲፈርዱ በልዑል ዓሥራተ ካሣ ይመረጣሉ። እሳቸው ራሳቸው ከለውጥ ፈላጊዎቹ አንዱ ነበሩና በአለቆቻቸው ፊት ሞገስን ለመላበስ ሲሉ ከታሪክና ከኅሊናቸው ጋር መጋጨትን አልወደዱም።

ይልቁንም ምርጫ አድርገው የዘየዱት ከአዲስ አበባ መሰወርን ነበር።

“የታሪክ አውራ የሆኑና የማከብራቸው [እነ ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይን] ሰዎች ላይ ዳኛ ሆኜ ልፈርድባቸው ስላልፈቀድኩ ከአዲስ አበባ ጠፍቼ ወደ ሐረር ሔጄ ተደበቅኩ” ይላሉ።    

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 2
General Mengistu Neway Source: Courtesy of public domain

ሌላኛው የሕይወት ጉዟቸው ውስጥ የገጠማቸው የታሪክ ምዕራፍ የየካቲት ‘66ቱ ሕዝባዊ አብዮት ክስተት ነው።

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ  የዘውድ ሥርዓት በአዲሱ የልጅ እንዳልካቸው መኮንን መንግሥት እጅ ሲገባ ባሕር ተሻግረው ይገኙ የነበረው አገረ አሜሪካ ነበር።

አዲሱ መራሄ መንግሥት ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ራሳቸው ለዶ/ር በረከት ስልክ መትተው እገዛቸውን እንደሚሹ ጠይቀዋቸዋል። ሆኖም የዶ/ር በረከት ምላሽ በልጃቸው የሕክምና እርዳታ መሻት ሳቢያ ‘አይቻለኝም’ የሚል ሆነ።

ይሁንና የልጅ እንዳልካቸው መንግሥት ሲያከትም፤ ወዳጃቸውና ዘመዳቸው ሌተና ጄኔራል አማን አንዶም የተተኪው የጊዜያዊው ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ሊቀመንበር በመሆናቸው ዳግም ወደ አገር ቤት ተጠሩ።

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 2
Lt. General Aman Andom Source: Courtesy of AT

የዘውድ ሥርዓቱን ባለ ሥልጣናት እንዲመረምሩም በደርግ የተቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ።

የዛሬው መነሻችን ከታህሳሱ የለውጥ እንቅስቃሴ ክሽፈት በኋላ የዳኝነት ስየማ ሂደት ላይ ነው።


Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Listen to our podcasts

Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now