Watch FIFA World Cup 2026™ LIVE, FREE and EXCLUSIVE

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 4

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 4

Emeritus Prof Bereket Habte Selassie Source: Courtesy of BHS

የክፍል አራት የፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ ግለ ሕይወት ትረካ መነሻ በቀድሞው የኢሕዲሪ መንግሥትና በአማጽያን ኃይላት መካከል ተካሂደው ለስኬት ያልበቁን የአትላንታ፣ ኬንያና ሎንዶን የሰላም ድርድር ጥረቶች ናቸው። ነገን አማትረው በማየትም፤ የአሰብ ጉዳይ በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ያሉ ችግሮች ሲፈቱ በድርድር አብሮ ተፈቺ ሊሆን እንደሚችል ያስባሉ።


ፕሮፌሰር በረከት በትናንቱ የኤርትራ ሕዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት መሪና ዛሬም ድረስ ለ፳፮ ዓመታት ኤርትራን በፕሬዚደንት እየመሩ ያሉትን ኢሳይያስ አፈወርቂን ማንነት በውል ለመረዳት እንደምን እንዳዳገታቸው ያነሳሉ።

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 4
Isaias Afewerki - President of Eritrea Source: Courtesy of GAC
“የኢሳይያስ አፈወርቅ ነገር ዕንቆቅልሽ ነው” ይላሉ።

ከኢሕዲሪ መንግሥት ውድቀት በኋላ ኤርትራ ለሉዓላዊት አገርነት በመብቃትዋ እንደ አገር ለመቆም ከሚያሿት ዋነኛ የመተዳደሪያ ሰነዶች መካከል ሕገ መንግሥት ነበርና የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አቆመች። 

ፕሮፌሰር በረከትም የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠቅላይ ዓቃቤነት የሥራ ተሞክሯቸውና ሲልም በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢራቅ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ናይጄሪያና አፍጋኒስታን ያበረከቱት የሕገ መንግሥት ረቀቃ አስተዋጽዖዋቸው ሚዛን ደፍቶ በፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቅ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሆነው ተሰየሙ።

Life and Legacy: Fikrou Kidane – Pt 4
From left to right Dr Yash Ghai, Dr Humam Hamoudi (President of Iraq's Constitutional Commission), Prof Bereket Habte Selassie, and Ms. Jill Cottrell (2005) Source: Courtesy of BHS

ከዓመታት ድካም በኋላ የሥራ ፍሬያቸውን ለአገሪቱ ፓርላማና ፕሬዚደንት አቀረቡ። ሆኖም ኤርትራ በሕገ መንግሥት ስትተዳደር የማየት ምኞታቸው ከቀን ሕልምነት አላለፈም። ኤርትራ ዛሬም ድረስ ሕገ መንግሥት የላትም።

Life and Legacy: Emeritus Prof Bereket Habte Selassie - Pt 4
Prof Bereket Habte Selassie in his office at the HQ of the Constitutional Commission Source: Courtesy of BHS
የሕዝባቸው ርዕይ ዕውን ባለመሆኑ “እኔንም ጨምሮ፤ ከነፃ አውጪነት ዘመን ጀምሮ እስከ አሁኑ የኤርትራ መንግሥት ድረስ ላለው ታሪካዊ ሁነት ሁላችንም ተጠያቂዎች ነን” ከሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።

Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Listen to our podcasts

Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now