ቃለ ምልልስ - አቶ ሀይለ ልኡል ገብረ ሰላሴ በዘንድሮው የአውስትራሊያ ቀን "ኦርደር ኦፍ አውስትራሊያ" የክብር ሽልማት ተሸላሚ

Ato Haileluel Gebreselassie Source: SBS Amharic
አቶ ሀይለ ልኡል ገብረ ስላሴ የአፍሪክውያን ቲንክ ታንክ መስራች አባል እና የወቅቱ ሊቀመንበር አንዲሁም በቪክቶርያ ፖሊስ የአፍሪካውያን ግብረ ሃይል ሰብሳቢ ፤ በዘንድሮው የአውስትራሊያ ቀን ፤የኦርደር ኦፍ አውስትራሊያ የክብር ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።የዚህን ሽልማት ሂደት የአውስትራሊያ የአገረ ገዥ መስሪያ ቤት የሚመራው ሲሆን ፡በየጊዜውም ከተለያዩ ቦታዎች የሚደርሱትን ጥቆማዎች በማጣራት እና የእማኞችን የድጋፍ ግባት በመመዘን ተገቢ ለሆኑ እጩዎች ሽልማቱን ያበረክታል። አቶ ሀይለ ልኡል ባለፉት ፪፭ አመታት በአውስትራሊያ ለቪክቶሪያውያን ማህበረሰብ አባለት እንዲሁም በአገር አቀፍ ደርጃ ከመንገስት ጋር ፤ በበጎ ፈቃደኝነት እና በመደበኛው ስራቸው ያበረከቱዋቸው አስተዋጻኦዎች ተመዝነው ለዚህ ታላቅ የክብር ሽልማት እንዳበቃቸው ነገረውናል። ይህ ሽልማት ተጨማሪ ሃላፊነቶችንም እንዲቀበሉ እና ማህበረሰቡንም ለማገልገል የበለጠ እንዲተጉ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል።
Share