Remembering Prof Alem Habtu

Prof Alem Habtu Source: Courtesy of AH
ፕሮፌሰር ዓለም ሐብቱ፤ በትግራይ ክፍለ ሃገር በእንደርታአውራጃ በሐርንቆ አምባ በግንቦት 1936 ተወልደው፤ ነሐሴ 30፣ 2008 በሃገረ አሜሪካ አርፈዋል። የቀብር ሥነ ሥር ዓታቸውም በኒው ዮርክ ከተማ ጳጉሜን 1፣ 2008 ተፈጽሟል። ፕሮፌሰር ዓለም፤ ባለትዳርና የሁለት ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ። በቀድሞው የኢትዮጵያ ተማሪዎች በሰሜን አሜሪካ ፕሬዝደንትነታቸውም የSBS የአማርኛ ፕሮግራም እንግዳ ሆነው፤ “ከተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ሰማያዊ ፓርቲ” በሚለው ልዩ ዝግጅታችን የሰሜን አሜሪካ ተማሪዎችን የትግል ታሪክ በዋቤነት ነቅሰዋል።
Share




