የውይይት መድረክ - የኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ አቅጣጫ ወዴት? ክፍል 1

Panel discussion Ethiopia's future Pt 1

Dr Semahagn Gashu (L), Geletaw Zeleke (C), and Dr Yohannes Gedamu (R) Source: Courtesy of SG, GZ, and YG

ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹ፤ በ Endicott ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶችና ዓለም አቀፍ ሕግ መምህር፣ ደራሲ ገለታው ዘለቀና ዶ/ር ዮሃንስ ገዳሙ፤ በ Georgia Gwinneett ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር፤ “የኢትዮጵያ የለውጥ አቅጣጫ ወዴት?” በሚለው የውውይት መድረካችን አጀንዳ ላይ ግለ አተያያቸውን ያንጸባርቃሉ። ደራሲ ገለታው ዘለቀ “ የዶ/ር ዐቢይ መንግሥት መሠረታዊ ችግር የለውጡ ፍኖተ ካርታ አለመኖር ነው። ወሳኝ በሆኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የግድ መያዝ አለብን ” ይላሉ። ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹ “ሊሂቃንን በሁሉም ጉዳዮች ላይ ያሳተፈ ብሔራዊ መግባባት ከሌለ፤ ለውጡ ካሁን በኋላ እስካሁን በሔደበት መንገድና ሂደት መቀጠል አይችልም” ሲሉ፤ ዶ/ር ዮሐንስ ገዳሙ “ሊሂቃን መደራደር ወይም መግባባት አለባቸው ስንል፤ ‘ሊሂቃኑ እነማን ናቸው?’ የሚለውን መጠየቅ መቻል አለብን። መደረግ አለበት የሚለውንና መሆን የሚችል የሚለውን ለያይተን መመልከትና መደረግ የሚችለውን እንደ ቅድመ ሁኔታ መውሰድ መቻል አለብን” በማለት አተያያቸውን ያጋራሉ።



Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service