ዛሬ እሑድ ኤፕሪል 24 በመላው ዓለም በዓለ ፋሲካ እየተከበረ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ውስጥም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በሙሉ በዓለ ትንሣኤው በድምቀት ተከባሪ ነው።
በዓሉን አስመልክቶም የሃይማኖት መሪዎች በዋዜማው የእንኳን አደረሳችሁ መንፈሳዊ መልዕክቶቻቸውን ለሕዝበ ክርስቲያኑ አስተላልፈዋል።
የበዓሉንም ዋነኛ ዕሳቤ አስመልክተው “የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የሰው ልጅ ኃጢአት የተሰረየበት ፣ ፍቅር የተገኘበትና መድኅን የተጎናፀፈበት ነው” ሲሉ አስገንዝበዋል።
ሕዝበ ክርስቲያኑ ዕለተ ፋሲካን በሐሴት ሲያከብር ለጉስቁልና የተጋለጡ፣ ለእርዛት የተዳረጉትንም በችሮታቸው በመጎብኘት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቶ ያለው የስላም መደፍረስም ሕዝባዊ ጥረቶች ታክለውበት አስቸኳይ እልባት እንዲበጅለት ጥሪ አቅርበዋል።

Residents at Kalyna aged care centre attending orthodox Easter service. Source: SBS