ቪክቶሪያ ውስጥ 723 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተያዙ 13 ሕይወታቸውን አጡ

***ሪጂናል ቪክቶሪያውያን እንደ ሜልበርናውያን ጭምብል አጥልቀው እንዲንቀሳቀሱ ተወሰነ

新冠疫情肆虐如何自保?

新冠疫情肆虐如何自保? Source: AAP

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት ሐሙስ 723 በኮሮናቫይረስ ሲጠቁባት 13 ሰዎቿም ሕይወታቸውን አጥተውባታል። ይህም በእጅጉ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

ሰኞ ዕለት ቪክቶሪያ ውስጥ በአንድ ነጠላ ቀን ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 532 ነበር።

ማክሰኞ ቁጥሩ ወደ 384 ሲወርድ ረቡዕ ወደ 295 አሽቆልቁሎ ነበር።

የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በአሁኑ ወቅት በሪጂናል ቪክቶሪያ 255 የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች መኖራቸውን ገልጠዋል። 

ይህንኑም ተከትሎ ማናቸውም የሪጂናል አውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑ በሙሉ ከእሑድ 11:59 pm ጀምሮ ከቤታቸው ሲወጡ ጭምብል የማጥለቅ ግዴታ እንዳለባቸው ፕሪሚየር አንድሩስ በዛሬው ዕለት አስታውቀዋል።

በዚህም መሠረት መላው የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከቤታቸው ሲወጡ ጭምብል ሳያጠልቁ መንቀሳቀስ አይችሉም።

እንዲሁም፤ የ Greater Geelong, Surf Coast, Moorabool, Golden Plains, Colac-Otway እና Queenscliff ነዋሪዎች ከሐሙስ 11:59pm ጀምሮ ቤታቸው ውስጥ እንግዳ ተቀብለው ማስተናገድ አይፈቀድላቸውም።

 


Share

Published

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ቪክቶሪያ ውስጥ 723 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተያዙ 13 ሕይወታቸውን አጡ | SBS Amharic