የነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ ረቂቅ ሕዝበ ውሳኔ ቀን ይፋ ሆነ

የሜዳ ቴኒስ ኮከቡ ራፋኤል ናዳል ከቴኒስ የመጠወር ውሳኔው ላይ በሩን ገርበብ አድርጎ ዘጋ።

FIRST NATIONS PEOPLES.jpg

Aboriginal people dance at Sydney Harbour, Australia, Nov. 11, 2020. Credit: Xinhua/Zhu Hongye via Getty Images

አንኳሮች
  • የ'እደግፋለሁ' ዘመቻ ፌብሪዋሪ መገባደጃ ላይ ይጀምራል
  • ረቂቅ ድንጋጌው ለፓርላማ ቀርቦ ክርክር ይካሔድበታል
  • ረቂቅ ድንጋጌው በወርሃ ሜይ በፓርላማ ይሁንታን አግኝቶ ፅድቅ እንዲቸረው ይጠይቃል
የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሚኒስት ሊንዳ በርኒ ድምፅ ለፓርላማ ሕገ መንግሥቱ እንዲሠፍር ለማስቻል ሕዝበ ውሳኔ በወርሃ ኦገስት መጀመሪያ ላይ ሊካሔድ እንደሚችል ገለጡ።

ሚኒስትሯ ከሲድኒ ሞሪኒንግ ሔራልድ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የ 'እደግፋለሁ' ዘመቻ ፌብሪዋሪ መገባደጃ ላይ እንደሚጀመርና ረቂቅ ሕጉ በወርሃ ማርች ለፓርላማ ውይይት እንደሚቀርብ ተናግረዋል።

አክለውም፤ ዘመቻውን ማንቀሳቀስ ከጀመርን በኋላ አገሪቱን ለለውጥ ዝግጁ እናደርጋለን፤ ረቂቅ ድንጋጌው በሜይ ላይ ይሁንታን አግኝቶ ካለፈ በኋላም ሕዝበ ውሳኔው ቀደም ካለ በኦገስት፤ ከዘገየም ኖቬምበር ላይ እንደሚካሔድ አመላክተዋል።

ቴኒስ

የሜዳ ቴኒስ ኮከቡ ራፋኤል ናዳል ቅዳሜ ዲሴምበር 31 ከካሜሩን ኖሪ ጋር ለዩናይትድ ዋንጫ በሲድኒ ኬን ሮዝዌል ኧሬና ባደረገው ግጥሚያ 3-6, 6-3, 6-4 ውጤት ተረትቷል።

ይህንኑ ሽንፈቱን ተከትሎ ከጋዜጠኞች ከቴኒስ ለመጠወር ያስብ እንደሁ ተጠይቆ ሲመልስ "የተሸነፍኩት ግጥሚያውን ነው፤ አለቀ" በማለት ከቴኒስ የመሰናበትና አለመሰናበት ጥያቄን አሌ ብሎ አልፏል።

 












Share

Published

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ ረቂቅ ሕዝበ ውሳኔ ቀን ይፋ ሆነ | SBS Amharic