የተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት እንዳለው በርካቶችን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ድንበር ለማድረስ ጭና ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ በመስጠሟ ከ 68 በላይ ስደተኞች ሕይወታቸው ተቀጥፏል፤ 74 ስደተኞች የደረሱበት አልታወቀም።
ሕይወታቸው ካለፈው ውስጥ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ናቸውም ብሏል።
አሶሽዬትድ ፕሬስ የ54ቱ ስደተኞች አስከሬን በባሕር ዳርቻ በአሳዛኝ ሁኔታ ወዳድቆ ነው የተገኘው።
የፍልሰተኞቹ ድርጅት እስካሁን 12 ሰዎች በሕይወት ተርፈው መገኘታቸውን ገልፆ፤ ሌሎች አስከሬኖችን እና በሕይወት የተረፉ ካሉ ለማግኘት ፍለጋው ይቀጥላል ብሏል።