ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር የሥራ ጊዜ ገደባቸውን አጠናቅቀው ተሰናበቱ

የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ያሰናበቱት፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎ ናቸው።

Bekele.png

Dr Daniel Bekele, Chief Commissioner of the Ethiopian Human Rights Commission (L) and Tagesse Chafo, Speaker of the House of Peoples' Representatives (R). Credit: ENA

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት ሰኔ 25 ቀን 2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ ነው፡፡

የሕግ ባለሙያና የሰብ ዓዊ መብቶች ተሟጓች የነበሩት ዳንኤል በቀለ፤ ቀደም ሲልም የሰብዓዊ መብቶች ተመልካች ድርጅት የአፍሪካ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ሆነው ሠርተዋል።

በዓለም አቀፍ ሕግ ሶስተኛ ዲግሪያቸውን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ሕግ ሰብዓዊ መብቶች ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከእንግሊዝ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በማኅበራዊና የአካባቢያዊ ልማት የተቀበሉት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው።

Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service