የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ ተካሒዶ ሳይጠናቀቅ በመቅረቱ በይደር ቀጠሮ ተለየ

በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር፤ ሰኔ 29 / ጁላይ 6 ባካሔደው የዙም ጠቅላላ ጉባኤ፤ ዓመታዊ ሪፖርቱን ለማኅበረሰቡ አባላት አቅርቧል። ከታዳሚ የማኅበረሰቡ አባላት በርካታ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ከማኅበረሰቡ የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላትም ምላሾች ተሰጥቶባቸዋል።

ተስፋዬስፋየ.png

Dr Tesfaye Yigzaw, President of the Ethiopian Community Association of Victoria. Credit: SBS Amharic

በተካሔደው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ዓመታዊው ሪፖርት የቀረበው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው ነው።

የማኅበሩ ፕሬዚደንት ባቀረቡት ሪፖርት፤
  • የተሠሩና በመሠራት ላይ ያሉ ክንውኖች
  • ዓመታዊ ሕዝባዊ ክብረ በዓላት
  • የስፖርት ክንዋኔዎች
  • ከፖሊስና የመንግሥት ባለ ስልጣናት ጋር የተካሔዱ ውይይቶች
  • የወጣቶች፣ ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የአዕምሮ ጤና
  • የፋይናንስ ሪፖርት
  • መልካም ዕድሎች
  • የአጋጠሙ ችግሮችና
  • ቀጣይ አቅጣጫዎችን
በአንኳርነት አንስተው ጠቅሰዋል።

በስብሰባው ወቅት ከታዳሚ የማኅበረሰቡ አባላት በዋነኛነት፤
  • የማኅበሩ ስምና ዓርማ ለውጥ አስፈላጊነት
  • በዙም ስብሰባ ማድረጉ መልካም ሆኖ ሳለ በአካል የአዳራሽ ስብሰባ ቢካሔድ
  • በሪፖርቱ ላይ ተግዳሮች ስለምን አልተገለጡም?
  • ሪፖርቱ የተሟላ አይደለም
  • ሪፖርቱ ላይ ዝርዝር የፋይናንስ ወጪና ገቢ ቢቀረብ
  • የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለመቀየር የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስፖንሰር አወዛጋቢነት
  • የአማራ ሕዝብ ሲጨፈጨፍ አንድም የተቃውሞ ደብዳቤ በሥርዓቱ ላይ ፅፋችሁ አይቼ አላውቅም
  • የተቃውሞ ሠልፍ ብታዘጋጁ
  • ተቋማዊ አሠራር ብታዳብሩ
  • ሪፖርቱ እስካሁን የሠራችሁትን ጠንካራ ሥራዎቻችሁንን አያንፀባርቅምና አጠንክራችሁ ግለጡት
  • የንቅናቄ፣ የግንኙነት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ቢሠሩ ጥሩ ነው
  • ማኅበሩ አሰባሳቢ መሆን አለበት
  • ማኅበሩ ላይ ጎልቶ መምጣት ያለበት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ናት
  • ተባብረን ማኅበሩን ብንደግፍ
  • ግላዊ ሽኩቻዎችን ወደ አደባባይ ባታመጡ

    የሚሉ ጥያቄዎችና አተያዮች ተንፀባርቀዋል።
ከታዳሚ የማኅበረሰብ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የማኅበሩ ሥራ አስፈፃሚ አባላት አቶ ንብረት ዓለሙ፣ ወ/ሮ እቴቱ፣ ወ/ት ገነት ማስረሻ፣ አቶ ኃይለሰማዕት መርሃጥበብና ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው ለስብሰባው የተመደበለት ሰዓት እያከተመ መሆኑን አመላክተው በቅደም ተከተል አጫጭር ምላሾችን በሰጡበት ወቅት፤
  • የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች አይደለንም
  • ከሲድኒ አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካይ በቅርብ ጊዜ ወደ አውስትራሊያ በረራ ሊጀምር በዕቅድ ላይ በመሆኑ ማብራሪያና ማስተዋወቂያ ለመስጠት ተጠይቀን ነበር፤ በሥራ አስፈፃሚ በኩል ተነጋግረንበት የቀረበውን ጥያቄ አለመቀበላችንን አስታውቀናል
  • በሥራ አስፈፃሚ አባላት ውስጥ የሃሳብ ልዩነቶች መኖራቸው መልካም ቢሆንም የግል ጥቅም ግጭቶችም አስባብ ናቸው
  • በግል ፖለቲካዊ አቋሞች ቢኖሩንም አጀንዳዎቻችን የሚያተኩሩት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ጥቅሞች ላይ ነው
በማለት አስረድተዋል።

ለተነሱት ጥያቄዎች ተገቢና አርኪ ምላሾችን ለመስጠት፤ ተከታይ ጥያቄዎችንና አተያዮችን ለማስተናገድ ስብሰባው ከወሰደው በላይ ጊዜን ስለሚጠይቅ 'እንቀጥል ወይንስ በሌላ ስብሰባ ተመልስን እንወያይበት?' የሚል ጥያቄ ለታዳሚዎች ቀርቦ ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንት ባሉ ጊዜያት ውስጥ ቀን ተቆርጦ ለተነሱና ታካይ ጥያቄዎችና አተያዮች ምላሾች እንዲሰጡ ከሚል ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

ቀጣዩ ስብሰባም በዙም እንደሚካሔድ፤ አመቺ ዕለትና ሰዓት በማኅበሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተመክሮበት ለማኅበረሰቡ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ተነግሮ ዓመታዊው ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቅቋል።






Share

Published

Updated

By Kassahun Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ ተካሒዶ ሳይጠናቀቅ በመቅረቱ በይደር ቀጠሮ ተለየ | SBS Amharic