ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ፀሐፊ፣ የኒውዮርክና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ፤ ወደ አገር ቤት እንዳይገቡ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማለፊያ እንዲመለሱ መደረጉ ተመልክቷል።
የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር መግባት መከልከል ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን፤ የእገዳው አስባብ ምን እንደሆነ ግና አክሎ አልተገለጠም።
በሌላም በኩል አግባብ ባላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ከፍተኛ አመራር አባሉን ከአውሮፕላን ማረፊያ እንዳያልፉ መታገድ አስመልክቶ እስካሁን ጉዳዪን አስመልክቶ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልተሰጠም።
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ዩናይድ ስቴትስ የሔዱት የጥምቀት በዓል ላይ መገኘትና የመንፈስ ልጆቻቸውን መጎብኘትን አክሎ፤ ሐዋሪያ ተግባራቸውን ለመፈፀም እንደሆነም በቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት በኩል ተነግሯል።