በቪክቶሪያና ሜልበርን መካከል ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነሳ

*** ከቤት ውጪ ሁሌም ጭምብል ማጥለቅን ግድ ይላል

Victoria has recorded nine straight days of zero coronavirus cases.

Victoria has recorded nine straight days of zero coronavirus cases. Source: AAP

የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት አንድም በኮሮናቫይረስ የተያዘ ወይም ለሕልፈተ ሕይወት ባልተመዘገበበት በዛሬዋ ዕለት እሑድ ኖቬምበር 8 በሪጂናል ቪክቶሪያና ሜልበርን መካከል ተጥሎ የነበረው ገደብ ዛሬ ከምሽቱ 11:59 pm ጀምሮ መነሳቱን አስታውቀዋል።

እንቃስቃሴና ጉብኝት

  • ከቤት ውጪ ከ25 ኪሎ ሜትር ርቆ ያለመሄድ ገደብም ተነስቷል
  • ሪጂናል ቪክቶሪያና ሜልበርንን ለይቶ የነበረው ገደብ ተከልቷል
  • ከሁለት የተለያዩ ቤተሰቦች ጥገኞቻቸውን ጨምሮ በየዕለቱ በጋር ወይም በተናጠል መገናኘት ይችላሉ
  • ቤት ውስጥ ሆነው መሥራት የሚችሉ ከሆነ ከቤት ሆነው መሥራት ይችላሉ
  • ከቤት ውጪ ሁሌም ጭምብል ማጥለቅን ግድ ይላል

ከ11.59pm ኖቬምበር 22 ጀምሮ

  • ጭምብል ማጥለቅ ላይ ለውጥ የለም
  • ቤት ውስጥ 10 ያህል ሰዎች መሰባሰብ ይችላሉ
  • ከቤት ውጪ  ከ12 ወራት በታች የሆኑትን ሳይጨምር 50 ሰዎች ከየትኛውም ቤተሰብ በጋራ ሊታደሙ ይችላሉ  

መስተንግዶ

ከ11.59pm ኖቬምበር 8 ጀምሮ

  • ምግብ ቤቶች፣ ሆቴሎች፣ ካፌዎችና ቡናቤቶች ቤት ውስጥ ከ40 ያልበለጠ (10 ሰዎች በአንድ ሥፍራ) በውጪ ከ70 ያልበለጠ (አንድ ሰው በሁለት ስኩየር ሜትሮች)

 

ሥነ ጥበብና መዝናኛ 

ከ11.59pm ኖቬምበር 8 ጀምሮ

  • ጋለሪዎች - በአንድ ሥፍራ ለ20 ሰዎች
  • ሲኒማ ቤቶች - በአንድ ሥፍራ ለ20 ሰዎች
  • ሙዚየሞች - በአንድ ሥፍራ ለ20 ሰዎች

 ከ11.59pm ኖቬምበር 22 ጀምሮ

  • የአካል እንቅስቃሴ ሥፍራዎች – ከ100 ያልበለጡ - በቡድን 20
  • የቤት ውስጥ ስፖርት – ከ100 ያልበለጡ - በቡድን 20
  • ትላልቅ የስፖርት ስፍራዎች – መያዝ ከሚችሉት መጠናቸው 25 ፐርሰንት ያላለፈ
  • የውጪ አካላዊ መዝናኛ – ከ500 ሰዎች ያልበለጠ - በቡድን 50
  • የቤት ውስጥ ዋና – ከ 50 ሰዎች ያልበለጠ
  • የውጭ ዋና  – ገደብ ሳይኖረው በአንድ ሰው 4 ስኩየር ሜትሮች 

 ማኅበረሰብና ቤተ እምነቶች

ከ11.59pm ኖቬምበር 8 ጀምሮ

  • የቀብር ሥነ ሥርዓቶች - ቤት ውስጥ ከ20 ያልበለጡ - በውጪ ከ50 ያልበለጡ ለቀስተኞች
  • የሠርግ ሥነ ሥርዓት ላይ የተደረገ ለውጥ የለም
  • ቤተ እምነቶች - ከ20 ያልበለጡ ምዕመናን በተጨማሪ አንድ የሃይማኖት መሪ - በውጪ ከ50 ያልበለጡ ምዕመናን በተጨማሪ አንድ የሃይማኖት መሪ

ከ11.59pm ኖቬምበር 22 ጀምሮ

  • የሠርግ ሥነ ሥርዓቶች ከ100 ታዳሚዎች ያልበለጡ በግል መኖሪያ ከ10 ያልበለጡ ታዳሚዎች
  • የቀብር ሥነ ሥርዓቶች እስከ 100 ለቀስተኞች በግል መኖሪያ ከ10 ያልበለጡ ለቀስተኞች 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now