ይህንኑ የኢትዮጵያ - አውስትራሊያ የቀጥታ በረራ ትልምን በማኅበራዊ ገፃቸው ይፋ ያደረጉት፤ ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ቀጣና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው።
ዋና ሥራ አስኪያጁ "ይህ የበረራ መስመር የሁለቱን ሀገራት መዳረሻዎች ማገናኘት ብቻ ሳይሆን፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ ከላቀ አይታክቴነት ጋር ክብርና ኩራትን ተላብሶ የአፍሪካና አውስትራሊያ የተሳለጠ ድልድይ ስለ መሆኑ ግዘፍ ነሺ መገለጫም ነው" ብለዋል።
ሆኖም፤ ትልሙን ዕውን ለማድረግ ከአከራይም ሆነ ሻጮች ኤይርባስ A350 ወይም ቦይንግ B787 የመንገደኞች አውሮፕላኖች እንደሚሹ አመላክተው የገበያ ጥሪም አቅርበዋል።
የ2024 ይፋ የአየር መንገድ መምሪያ የመንገደኞች ትራፊክ ዳታ ትንተናዎች እንዳመላከቱት ከሆነ በአዲስ አበባና ሜልበርን የመንገደኞች ደርሶ መልስ ጉዞዎች 6,000፣ ብሪስበንና ፐርዝ እያንዳንዳቸው 1,000 ሲሆን የሲድኒ መንገደኞች ዳታ ከ1,000 ያነሰ በመሆኑ እንዳልታከለ ተገምቷል።
ከአውስትራሊያ ዋነኛ ከተሞች ውስጥ ሜልበርን አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፤ እንዲሁም የበርካታ አፍሪካውያን - አውስትራሊያውያን መኖሪያ ናት።
ከአዲስ አበባ ሜልበርን የበረራ መስመር 6,495 ኖቲካል ማይልስ ወይም 12,029 ኪሎ ሜትሮች ነው።
የኢትዮጵያ አውሮፕላኖች ከኢትዮጵያ ተነስተው አውስትራሊያ የዘለቁት በሁለት ታሪካዊ ወቅቶች ነው።
አንደኛው፤ በ1956ቱ የሜልበርን ኦሎምፒክ ወቅት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችንና አስተባባሪዎችን ይዛ የመጣችው ጢያራና
በቀጣይነትም፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አውስትራሊያን በጎበኙበት ወቅት አውስትራሊያ ያረፉባት አውሮፕላን ናት።

Emperor Haile Selassie on his 1968 visit to Australia (Images courtesy National Archive of Australia and the Crown Council of Ethiopia) Source: (Images courtesy National Archive of Australia and the Crown Council of Ethiopia) Credit: Emperor Haile Selassie on his 1968 visit to Australia (Images courtesy National Archive of Australia and the Crown Council of Ethiopia) Source: (Images courtesy National Archive of Australia and the Crown Council of Ethiopia)