ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

የተቋሙ ደንበኞች ቁጥር 78 ነጥብ 3 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 75 ነጥብ 6 ሚሊዮኑ የሞባይል ድምጽ ተጠቃሚ ናቸው። የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥርም 40 ነጥብ 4 ሚሊዮን ደርሷል።

Ethio Telecom.png

Credit: D.Kebede

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተቋሙን አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ ተቋሙ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል።

ገቢው ካለፈ በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ21 በመቶ ወይም 16 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል። ገቢው ከእቅድ በላይ 103 ነጥብ 6 በመቶ ሆኗል። በዚህም 21 ነጥብ 79 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘትም ችሏል ብለዋል።

ከገቢው 39 ነጥብ 4 በመቶው ከድምጽ አገልግሎት የተገኘ መሆኑን ገልጸው፤ 27 ነጥብ 7 በመቶው ከዳታና ኢንተርኔት የተገኘ ነው። ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞች ቁጥርን ካለፈው ዓመት በ8 ነጥብ 9 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል።

 የቴሌብር ደንበኞት ቁጥርም 47 ነጥብ 55 ሚሊዮን መድረሱን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ አንድ ነጥብ 81 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር ተከናውኗል።

 አገልገሎቱ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ 2ነጥብ55 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማንቀሳቀስ መቻሉንም ጠቁመዋል።

Share

Published

Updated

By Demeke Kebede
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ | SBS Amharic