ፖሊስ፤ በሲድኒ ቦንዳይ የገበያ ማዕከል የስለት ጥቃት ሳቢያ ስድስት ሰዎች ሞተዋል፣ በርካቶች 'በፅኑዕ' ቆስለዋል
ለጊዜው ማንነቱ ያልተገለጠ አንድ ግለሰብ የዘጠኝ ወር ሕፃን ልጅን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን በስለት ወግቶ ያቆሰለ ሲሆን ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ ግለሰቡም በአንዲት የፖሊስ ሠራዊት አባል ተገድሏል።
1 min read
Published
Updated
By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS
Skip to article contentShare this with family and friends
ዛሬ ቅዳሜ ኤፕሪል 13 / ሚያዝያ 5 ከቀትር በኋላ ሲድኒ ቦንዳይ ጁንክሽን ዌስትፊልድ የገበያ ማዕከል ባደረሰው የጩቤ ጥቃት በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውንና ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አስታወቀ።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ አምቡላንስ በበኩሉ አንድ የዘጠኝ ወር ሕፃንን ጨምሮ ዘጠኝ የቆሰሉ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል ማጓጓዙን ገልጧል።
Credit: Photo by DAVID GRAY/AFP via Getty Images ከቆሰሉትም ውስጥ የተወሰኑቱ በብርቱ ወይም በፅኑዕ የቆሰሉ መሆኑ ተመልክቷል።
ፖሊስ ምርመራ እያካሔደ መሆኑንና ጥቃት ፈፃሚው ግለሰብ ብቻውን ጥቃቱን የሰነዘረ በመሆኑ ተያያዥ ስጋት የሌለ መሆኑን ገልጧል።
Families walk out of the Westfield Bondi Junction shopping mall after a stabbing incident in Sydney on 13 April, 2024. Credit: Getty / David Grayአክሎም፤ የጥቃት ፈፃሚው ግለሰብ ማንነትና ጥቃቱን ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳው ለጊዜው በውል ያልታወቀ መሆኑን አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ በበኩላቸው በክስተቱ ጥልቅ ሐዘን የተሰማቸው መሆኑን ገልጠዋል፣ ለቤተሰቦች መፅናንትንና ጥቃቱን ለገቱት የፖሊስ መኮንንና አገልግሎት ለሰጡ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበርዋል።