ድርጅቱ ሀቅ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን "ተስፋለም በእሥር ላይ በቆየባቸው ባለፉት ቀናት አስፈላጊውን ትብብር" ላደረጉ ሁሉ በማለት ምስጋና አቅርቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችሎት ትናንት ሐሙስ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም "የሥር ፍርድ ቤቶች የጋዜጠኛውን የዋስትና መብት መጠበቃቸውን መሠረታዊ የሕግ ጥሰት ያልተፈፀመበት እና ሕግን የተከተለ ሆኖ ስላገኘነው" ሲል የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ አጽንቷል።
ይሁንና ጋዜጠኛው ትናንት ሳይፈታ እሥር ቤት አድሯል።
ተስፋለም ከእሥር እንዲለቀቅ የሙያ ማኅበራት፣ ሲቪክ ድርጅቶች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ጉዳዩ ያገባናል ያሉ ሁሉ ሲወተውቱ ቆይተዋል።
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ "ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨት" በሚል ተጠርጥሮ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው እሑድ ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ነበር።