አዲሱ የኬንያ ተመራጭ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ ዛሬ ሴፕቴምበር 13, 2014 / መስከረም 3, 2015 በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ በካሳራኒ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተገኝተው ቃለ መሐላ በመፈፀም 5ኛው የኬንያ ፕሬዚደንት ሆነዋል።
የእሳቸውን ቃለ መሐላ ተከትለውም ምክትላቸው ሪጊታ ጋቻዎ ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።
በፕሬዚደንት ሩቶ በዓለ ሲመት ላይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የዑጋንዳ ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ፣ የሩዋንዳው ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜና የታንዛኒያ ፕሬዚደንት ሳሚያ ሱሉሁ፣ ሌሎች ርዕሰ ብሔሮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።