በቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ የተጠረጠረ ግለሰብና አንድ ታዳሚ ተገደሉየቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትና የሪፐብሊካን ፓርቲ 2024 ፕሬዚደንታዊ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ቅዳሜ ዕለት በፔንሲልቫኒያ የምረጡኝ ዘመቻ ንግግር እያደረጉ ሳለ ነው።Republican presidential candidate former President Donald Trump is helped off the stage at a campaign event in Butler, Pa., on Saturday, July 13, 2024. Source: AP / Gene J. Puskar/AP1 min readPublished 14 July 2024 11:45amUpdated 14 July 2024 11:49amBy Kassahun Seboqa NegewoSource: SBSSkip to article contentShare this with family and friendsCopy linkShareየአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በቀድሞው ፕሬዚደንት ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በዶናልድ ትራምፕ ልዩ የደህንነት ጥበቃ አባላት መገደሉንና የአንድ ታዳሚ ግለሰብ ሕይወት መቀጠፉንም ገልጠዋል። ባለስልጣናቱ አክለውም ሁለት የምረጡኝ ዘመቻ ታዳሚዎች መቁሰላቸውንም አክለው ተናግረዋል። በወቅቱ በርካታ የተኩስ ድምፆች ተሰምተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባይደን ክስተቱን አውግዘው ለቀድሞው ፕሬዚደንት ደህንነት እንደሚፀልዩ ገለጠዋል። የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚም ክስተቱን አውግዘዋል። Share