በ2011 የኩዊንስላንድ የሕዝብ መወሰኛ ምክር ቤት አባል የሆኑት ላሪሳ ዎተርስ ለመሪነት የበቁት፤ የቀድሞው ግሪንስ ፓርቲ መሪ አዳም ባንድት ሜይ 3 ቀን 2025 በተካሔደው የፌዴራል ምርጫ ወቅት የሜልበርን የሕዝብ ምክር ቤት ወንበራቸውን በማጣታቸው ነው።
ለግሪንስ ፓርቲ መሪ በተወዳዳሪነት ቀርበው የነበሩት ሴናተር ፋሩቂ የቀድሞ አመራር ኃላፊነታቸውን በመያዝ በምክትል መሪነት ዳግም ተመርጠዋል።

(Left to right) Greens Senator Penny Allman-Payne, deputy leader Mehreen Faruqi, party leader Larissa Waters, Senator Sarah Hanson-Young, and Senator Nick McKim. Credit: AAP / Joel
አዲሷ የግሪንስ መሪ ፓርቲያቸው ቀደም ሲል ሲገፋቸው በነበሩ ፖሊሲዎቹ እንደሚቀጥል ያመላከቱ ሲሆን፤ የፖሊሲ ቅደም ተከተላቸው የአየር ንብረት ለውጥ፣ ተፈጥሯዊ ሕግ፣ መኖሪያ ቤት፣ የአገልግሎት ገንዘብ ድጎማና ፍልስጣኤም እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።
የዘንድሮውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ፤ የግሪንስ ፓርቲ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት 11 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1 የምክር ቤት ወንበሮችን ለማሸነፍ የበቃ ሲሆን፤ በላይኛው ምክር ቤት የስልጣን ሚዛን አስጠባቂ ለመሆን በቅቷል።