የቪክቶሪያ ተጠባባቂ ፕሪሚየር ጄምስ ሜሊኖ ሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው የነበሩት የኮሮናቫይረስ ገደቦች ከነገ ሐሙስ ጁን 17 ከምሽቱ 11.59pm ጀምሮ እንደሚረግቡ ዛሬ አስታውቀዋል።
በዚህም መሠረት፤
ማኅበራዊ
- ቤትዎ ውስጥ በየቀኑ ሁለት ጎብኚዎችዎን ሊያስተናግዱ ይችላሉ
- ከቤት ውጪ በቡድን እስከ 20 ሰዎች መሰባሰብ ይፈቀድላቸዋል
የኪሎ ሜትሮች ገደብ
- ቀደም ሲል ከመኖሪያ ቤትዎ ከ25 ኪሎ ሜትሮች ርቀው በላይ እንዳይጓዙ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተንስቷል።
- የሜልበርን ነዋሪዎች ወደ ሪጂናል ቪክቶሪያ መጓዝ ይችላሉ።
የፊት ጭምብሎች
- በቤት ውስጥ የ1 ነጥብ 5 ሜትሮች ርቀትን ለመጠበቅ በማይቻልባቸው ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር የፊት ጭምብል ለማጠለቅ ግዴታ አይኖርም።
የምግብና መስተንግዶ ሥፍራዎች
- የምግብና መስተንግዶ ግልጋሎት ሰጪዎች አንድ ሰው በሁለት ስኩየር ሜትር ርቀት ማስተናገድ ይችላሉ።
- አካላዊ እንቅስቃሴ ማካሄጃ፣ የቤት ውስጥ መስተንግዶ ሰጪዎች ግልጋሎቶችን መስጠት ይጀምራሉ።