SKIP TO MAIN CONTENT

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ

የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ30 ሺሕ ብር ዋስትና በዛሬዉ ዕለት ከእስር መፈታቱ ታውቋል።

Journalist Temesgen Desalegn.jpg
Journalist Temesgen Desalegn. Credit: PR

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report

Source: SBS


Skip to article content

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ህገ መንግስታዊ ችሎት ትላንት ኀዳር 6 ቀን 2015 በዋለዉ ችሎት ጋዜጠኛው በ30 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ቢወስንም የቂልንጦ ማረሚያ ቤት ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ማደሩ ይታወቃል።

ዛሬ ኀዳር 7 ቀን 2015 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለ176 ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ መፈታቱን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now