ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ አባልነት ተመረጠች

*** የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ትግራይን አስመልክቶ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች በጋራ ያወጡት ሪፖርት ያሳስበኛል ሲል በድጋሚ አነሳ

News

Food donated by the World Food Program (WFP). Source: Getty

ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል ሆና መመረጧን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። 

የሥራ አስፈፃሚ አካሉ ከ36 የተመድ አባል መንግሥታት የተውጣጣ ነው። 

ቦርዱ ለመንግሥታት ድጋፍን ያደርጋል፣ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ይጠቁማል፣ እንዲሁም የተመድ የምግብ እርዳታ ቅርንጫፎችን ተግባራት ይቆጣጠራል። 

ዩናይትድ ስቴትስ ሰብዓዊ መብቶች

ዩናይትድ ስቴትስ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች በጋራ ያወጡት ሪፖርት ግኝት ላይ በተለይም የዘር ማፅዳት ድርጊት መጠነ ስፋት በእጅጉ እንዳወከው ገልጧል። 

ኣክሎም፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ዝርያ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ምዕራብ ትግራይ ውስጥ ለሕይወት አስጊ በሆነ መልኩ ለዕገታ መዳረግ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሶ፤ በእገታ ላይ የሚገኙት በአስቸኳይ እንዲለቀቁና ዓለም አቀፍ ተመልካቾች ተቋማቱን የመጎብኘት ሙሉ ፈቃድ እንዲኖራቸው ጠይቋል።

በማያያዝም፤ ጭካኔ የተመላባቸው የአመፅ ድርጊቶችን የፈፀሙ ማናቸውም ወገኖች ተጠያቂ እንዲሆኑና ተአማኒነት ያላቸው ምርመራዎችም እንዲካሔዱ ጥሪ አቅርቧል።

እንዲሁም፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ ክልላዊ ባለልጣን የተወሰዱትን የግጭት የማቆም የአቋም መግለጫዎችና ሕይወት አዳኝ አቅርቦቶችን የያዙ ቅልፈቶች ወደ ትግራይ የመዝለቅ ጅማሮ በመልካም ጎኑ እንደሚመለከተው አስታውቋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በድጋሚ የውጭ ኃይላት ከኢትዮጵያ፤ የክልላዊ መንግሥት ባለስልጣናትም ከጎረቤት ክልሎች የፀጥታ ኃይሎቻቸውን እንዲያስወጡ ጥሪ ማቅረቧንም ይፋ አድርጓል።     

 

 


1 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now