ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው የነበሩ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ረገቡ

*** በሜልበርን ነዋሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ከቤት ውጪ ከ5 ኪሎ ሜትሮች በላይ ያለመሔድ ገደብ ተነስቶ በ25 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ተገድቧል

Amharic News 18 October 2020

Victorian Premier Daniel Andrews has announced further changes to the state's coronavirus restrictions. Source: AAP

የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ተጥለው የነበሩ ገደቦች መላላታቸውን አስታወቁ።

በዚህም መሠረት ከዛሬ እሑድ ኦክቶበር 18 ከምሽቱ 11.59 ሰዓት ጀምሮ፦

ማኅበራዊ

  • በሜልበርን ነዋሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ከቤት ውጪ ከ5 ኪሎ ሜትሮች በላይ ያለመሔድ ገደብ ተነስቶ በ25 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ተገድቧል
  • ከቤት ለመውጣት አንዳችም የጊዜ ገደብ የለም
  • ከቤት ለመውጣት አራቱ ምክንያቶች (ሥራ፣ ትምህርት ቤት፣ ሕክምናና የክብካቤ ግልጋሎት) እንዳሉ ይቀጥላሉ
  • ከቤት ውጪ የሁለት ቤት ሰዎች እስከ ከ10 ሳይበልጡ መሰባሰብ ይችላሉ
  • ወደ ገበያ ለሸመታ ለመሔድ የቤተሰብ አባላት ቁጥርና በቀን የሸመታ ጊዜ ገደብ የለም   
 ጤናና ግላዊ ክብካቤ      

  • የፀጉር ቤቶች ጥብቅ ደንቦችን ተከትለው ክፍት ይሆናሉ
  • የቤት ውስጥ መዋኛ ሥፍራዎች ከጤና ባለሙያ ጋር በመሆን አንድ - ለአንድ በመሆን ለሃይድሮቴራፒ ክፍት ይሆናሉ
  • ከጤና ጋር ተያይዞ እስካሁን ግልጋሎት በመስጠት ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎች የፊት-ለፊት ግልጋሎቶችን መስጠት ይችላሉ
  • የፊት ጭምብል የመልበስ ድንጋጌ በሥራ ላይ መዋሉን ይቀጥላል  

መዝናኛ

  • ጎልፍ የክለብ ክፍሎችን ሳያካትት ክፍት ይሆናል
  • ስኬት ፓርኮች ክፍት ይሆናሉ
  • የውጪ መዋኛዎች 30 ያህል ዋነተኞች ያስተናግዳሉ
  • ቴኒስ የክለብ ክፍሎችን ሳያካትት ክፍት ይሆናል 

ጉዞ

  • ሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ እስከሚሆኑ ድረስ ከሜልበርን ወደ ሪጂናል ቪክቶርያ ያለ ፈቃድ መሔድ አይቻልም

ትምህርት ቤት 

  • ከኦክቶበር 26 ጀምሮ ከ8-10ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ይመለሳሉ

ከሁለት ሳምንታት በኋላ

  • ከኖቬምበር 1 ከምሽቱ 11.59 ሰዓት ጀምሮ ሁለት ሰዎች ከነልጆቻቸው ወደ ሌሎች ሰዎች በቀን አንድ ጊዜ ሄደው መጎብኘት ይችላሉ
  •  ከቤት ለመውጣት ተጥለው ያሉ አራቱ ምክንያቶች (ሥራ፣ ትምህርት ቤት፣ ሕክምናና የክብካቤ ግልጋሎት) ከኖቬምበር 2 ጀምሮ ይነሳሉ
  • ቤት ውስጥ ከ20 ከቤት ውጪ ከ50 ያልበለጡ ሰዎች (እንደ ቦታው ጥበትና ስፋት) ካፊዎች፣ ሬስቶራንቶች ውስጥ መስተናገድ ይችላሉ። የችርቻሮ፣ የውበት ሳሎንና ግላዊ ግልጋሎቶች ክፍት ይሆናሉ።
  • ከ20 ያልበለጡ ምዕመናን የውጭ ሃያማኖታዊ ስብስብ ማድረግ ይችላሉ።
  • ከ10 ያልበለጡ ሰዎች ሠርግ ላይ ይታደማሉ
  • ከ20 ያልበለጡ ለቀስተኞች የቀብር ሥነ ሥርዓት መገኘት ይፈቀድላቸዋል
  •  በውጭ የመዝናኛ ሥፍራዎች ከ50 ያልበለጡ ወይም የማይንቀሳቀሱ መቀመጫዎች ባላቸው ከ25 ያልበለጡ ሰዎችን መስተናገድ ይችላሉ 
*** የቫይረሱ ተዛማችነት ቁጥር እያሽቆለቆለ ከመጣም ከኖቬምበር 1 ከምሽቱ 11.59 ሰዓት በፊት የገደቦች ማርገቢያ ለውጦች ይደረጋሉ።

ቪክቶሪያ ውስጥ በዛሬው ዕለት ሁለት ሰዎች ብቻ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን አንድም ሕይወት ለህልፈት አልበቃም።

የቪክቶሪያ የ14 ቀናት የኮሮናቫይረስ ተዛማች ቁጥር 7.5 ሲደርስ የሪጂናል ቪክቶሪያ 0.5 ደርሷል።


 

 


 
 


 



Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው የነበሩ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ረገቡ | SBS Amharic