ቻይናና ሰለሞን ደሴቶች የፀጥታ ትብብር ውል ስምምነት ላይ ደረሱ

*** የሁለቱ አገራት የፀጥታ ትብብር ውል ስምምነት የፓስፊክ የኃይል ሚዛንን ያዛባል የሚል ስጋት በአውስትራሊያ፣ ኒውዚላንድና ዩናይትድ ስቴትስ ዘንድ አሳድሯል።

News

中國和索羅門群島已正式簽署雙邊安全合作框架協議。圖為2019年10月,中國國家主席習近平在北京會見索羅門群島總理蘇加瓦瑞。 Source: Getty

ቻይናና ሰለሞን ደሴቶች ዛሬ የፀጥታ ትብብር ውል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አሳወቁ።

ውሉ ደቡብ ፓስፊክ ላይ ለቻይና ባሕር ኃይል ጦር ሠፈር ምሥረታ በር ሊከፍት ይችል ይሆናል የሚል ስጋትን በአውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድና ዩናይትድ ስቴትስ ዘንድ አሳድሯል። 

በሁለቱ አገራት ዘንድ የፀጥታ ውል ስምምነት ላይ መደረሱን ቤጂንግ ላይ ይፋ ያደረጉት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ናቸው።

አቶ ዌንቢም የትብብር ውል ስምምነቱ ቤጂንግ  ከሆኒያራ ጋር ማኅበራዊ ሥርዓትን በማስፈን፣ የሰዎች ደኅነነት ጥበቃ፣ እርዳታ፣ የተፈጥሮ አደጋዎችን መከላከል እና የብሔራዊ ፀጥታ ጥበቃ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጠዋል። 

የሰለሞን ደሴቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀርሚያህ ማኔሌ የትብብር ውል ስምምነቱ በፊርማ መጽደቁን ለABC በአጭር የስልክ ፅሁፍ መልዕክት አረጋግጠዋል። 

በመልዕክታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ማናሴህ ሶጋቫሬ ስምምነቱን አስመልክተው በመጪዎቹ ቀናት ይፋ መግለጫ እንደሚሰጡበት ገልጠዋል።

የሌበር ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ሴናተር ፔኒ ዎንግ የፓስፊክ ቀጣና በጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አመራር ቸል መባሉንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራችውን እንኳ ወደ ደሴቲቱ መዲና ለመላክ አለመከጀላቸውን አጣቅሰው ብርቱ ትችት ሰንዝረዋል።

News
Source: P.Wong

ከስምምነቱ የፊርማ ፀደቃ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የአውስትራሊያ የዓለም አቀፍ ልማትና የፓስፊክ ሚኒስትር ዜድ ሰሰልጃ ወደ ሆኒያራ አምርተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ማናሴህ ሶጋቫሬ ጋር በመገናኘት የአውስራሊያን አቋም አስረድተዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ትብብሩ ግልፅነት የተመላው እንደሚሆንና ሌላ ሶስተኛ አገርን ዒላማ እንደማያደርግ ተናግረዋል። 


2 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now