SKIP TO MAIN CONTENT

ጨፌ ኦሮሚያ የአቶ ታየ ደንደአን ያለመከሰስ መብት አነሳ

የአቶ ታየ ደንደአ በምክር ቤት አባልነት ያለመከሰስ መብት የተገፈፈው ጨፌ ኦሮሚያ ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሔደበት ወቅት ነው።

Taye D.png
Former state minister for peace, Taye Dendea. Credit: ENA

1 min read

Published

By Stringer Report

Source: SBS


Skip to article content

የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤ ከውሳኔ ላይ የደረሰው የካቲት 11 ለስድስተኛ ዓመት ሶስተኛ የሥራ ዘምን በተሰየመበት ዕለት ነው።

የአቶ ታየ ያለመከሰስ መብት የተገፈፈውም በ439 የድጋፍና 14 ድምፀ ተአቅቦ ውጤት መሠረት ነው።

የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ታየ ደንደአ በተጠርጣሪነት በእሥር ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ለእሥራት የተዳረጉትም በፌዴራል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ነው።

ግብረ ኃይሉ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ባወጣው መግለጫ አቶ ታየ "ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር በተሳሰር ለጥፋት ተልዕኮ በሕቡዕ ሲሰራ ተደርሶበታል" ብሏል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now