የሌበር ፓርቲ የቻይናና ሰለሞን ደሴቶች የፀጥታ ስምምነት 'አስከፊው የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ክሽፈት' ነው አለ

*** የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቻይናና ሰለሞን ደሴቶች መካከል የተካሔደው የፀጥታ ስምምነት ጂኦስትራቴጂካዊ ተግዳሮቱ ብርቱ መሆኑን አንስተው ክንዋኔውም ቅሬታና ስጋት ያሳደረባቸው መሆኑን ገለጡ።

News

Senator Penny Wong (L), and Australian Foreign Minister Marise Payne. Source: Getty

የሌበር ፓርቲ ትናንት ማክሰኞ ምሽት በቻይናና ሰለሞን ደሴቶች መካከል ለፊርማ የበቃው የጸጥታ ትብብር ስምምነት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ክሽፈት እንደሆነ ጠቅሶ በፌዴራል መንግሥቱ ላይ የከረረ ትችት ሰነዘረ። 

ከአውስትራሊያ 1,600 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የምትገኘዋ የሰለሞን ደሴቶች ከቻይና ጋር ያደረገችው ስምምነት የቀጣናውን ደኅንነት እንደሚያሳሳ የሌበር ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፔኒ ዎንግ ገልጠዋል። 

ሴናተር ዎንግ የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ፖሊስ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ እንዲህ ያለ የከፋ ክሽፈት የገጠመው በጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አመራር ወቅት እንደሆነ አመላክተው፤ ይህም "የቀጣናው ደኅንነት የሳሳ እንዲሆንና አውስትራሊያንም የሚገጥሟት የአደጋ ስጋቶች የገዘፉ ይሆናሉ" ሲሉ አሳበዋል። 

አያይዘውም፤ መንግሥት ፈጠኖ ሊንቀሳቀስ ይገባ እንደነበርና የወቅቱ የዓለም ስትራቴጂያዊ የአደጋ ስጋቶች ሁኔታ እጅጉን አሳሳቢ መሆኑን አመላክተዋል።

ይሁንና የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜሪዝ ፓይን የፌዴራል መንግሥቱ ላይ የሚሰነዘሩት ትችቶች "ለራሳቸው ውሳኔዎች ላይ የሚደርሱ መንግሥታት ሉዓላዊ ውሳኔዎችን" ያገናዘበ እንዳልሆነ በማመላከት በመንግሥታቸው ላይ የተሰነዘሩ ነቀፌታዎችን ተከላክለዋል። 

ሆኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በቻይናና ሰለሞን ደሴቶች መካከል የተካሔደው የፀጥታ ስምምነት ጂኦስትራቴጂካዊ ተግዳሮቱ ብርቱ መሆኑን አንስተው ክንዋኔውም ቅሬታና ስጋት ያሳደረባቸው መሆኑን ገልጠዋል። 

ስምምነቱ ለፊርማ ከመብቃቱ በፊት ግልፅነት በተመላበት መንገድ ከቀጣናው አገራት ጋር በስፋት ከፓስፊክ ቤተሰብ (አውስትራሊያና ኒውዝላንድን ጨምሮ) ጋር ሊመከርበት ይገባ እንደነበርም አንስተዋል። 


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now